📍እምነት እና ጥርጣሬ
እምነት ኖሮህም ቢሆን ከጥርጣሬ ጋር መታገል ትችላለህ።
📖 (ማር 9፥24)
📍ሰላም እና ጭንቀት
ጭንቀት እየተሰማህም ቢሆን የእግዚአብሔርን ሰላም ማግኘት ትችላለህ።
📖 (መዝ 94፥19)
📍ደስታ እና ድብርት
በድብርት ውስጥ እያለፍክም ቢሆን የደስታ ጊዜያትን ማግኘት ትችላለህ።
📖 (ሰቆ.ኤር 3፥20-23)
ሁለት ተቃራኒ የሚመስሉ ነገሮች በአንድ ጊዜ እውነት ሊሆኑ ይችላሉ። ዛሬ ሁለቱንም (እነዚህን ተቃራኒ ስሜቶች) ይዘህ ከሆነ ብቻህን አይደለህም ፤ እንዲሁም አልወደቅህም።
እግዚአብሔር የሚያገኝህ በዚያ ውጥረት ውስጥ እንጂ፣ ውጥረቱን አልፈህ ማዶ ስትደርስ ብቻ አይደለም።
👏በነገር ሁሉ የጌታ ጸጋ ይርዳን 👋
17
7
4
4
2
1May 2, 2026 1.5K 3