እኛ ያመንን፡ እውነተኛ እርካታ ያለን ነን።
ማጣትን ዐውቀዋለሁ፤ ማግኘትንም ዐውቀዋለሁ። ብጠግብም ሆነ ብራብ፣ ባገኝም ሆነ ባጣ፣ በማንኛውም ሆነ በየትኛውም ሁኔታ ያለኝ ይበቃኛል የማለትን ምስጢር ተምሬአለሁ።
ፊል 4፡12
እኛ ያመንን ረክተናል ወይም እውነተኛ እርካታ አለን የምንለው ነገሮች ስለተመቻቹ ወይም አማኝ ስንሆን ቁሳዊ ብልጽግናን ስለተቀበልን አይደለም ፤ ሚባልም ነገር የለም ፤ ግን እኛ በእውነት ረክተናል የምንለው የሚያስፈልገንን ሁሉ እንደባለጠግነቱ በክርስቶስ በሚሞላብን ላይ የሚያስፈልገንን ሁሉ እንደሚሰጠን ባለን እምነት ነው። ስለዚህ ነገሮች እንደፈለጉ ቢሆኑ ብናጣም ሆነ ብናገኝ ፣ ብንጠግብም ሆነ ብንራብ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ያለን ጌታ ይበቃናል።
ጸሎት፡
ጌታ ኢየሱስ ሆይ በአንተ አቅራቢነት ላይ ያለኝን መተማመን እንድትጨምርልኝ ብሎም በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብሆን ኅይልን በምትሰጠኝ በአንተ ሁሉን መቋቋም እንድችል አስለምደኝ። አሜን!
OUR SOCIALS:
INSTAGRAM | YOUTUBE | TIKTOK
#እኛ_ያመንን
#digital_week
#digital_strategy
#astu_ecsf














