ከእግዚአብሔር ጋር በጽኑ እንዴት መገናኘት ይቻላል? 👀
አብዛኛው ሰው ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይፈልጋል... ነገር ግን እርሱን በእውነት ለማግኘት በቂ ጊዜ ወስዶ ፍጥነትን አይቀንስም።
ከእግዚአብሔር ጋር በጽኑ መቆራኘት ማለት ሃይማኖተኛ መሆን ብቻ አይደለም ፤ ይልቁንም እውነተኛ መሆን ነው።
▫️ የበለጠ ንቁ መሆን
▫️ የበለጠ ራስን አሳልፎ መስጠት
ከእግዚአብሔር ጋር ወዳጅነት የሚመጣው በዝግመተ ለውጥ ሳይሆን በጥረት ነው። እንዲህ ነው የሚገነባው፦
📍ጥዋትህን በአግባቡ ጀምር
ስልክህን ከመንካትህ በፊት። በዕለቱ ግርግርና ረብሻ ውስጥ ከመግባትህ በፊት።
▫️ ጸልይ
▫️ መጽሐፍ ቅዱስህን ግለጥ... ለ5 ደቂቃ ቢሆን እንኳ
▫️መደበኛነት (Consistency) > ከፍተኛ ጥረት (Intensity)
📍በስሜት ሳይሆን በዲስፕሊን (ሥርዓት) ተመራ
ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ግንኙነት በዕለት ተዕለት ልምምድህ የሚቀረጽ ነው። ቀንህን የምትጀምርበት መንገድ ፣ ቀኑን ማን እንደሚመራው ይወስናል።
ትኩረትህን የሚከፋፍሉ ነገሮችን አስወግድ
▫️ ልምዶችህን አጽዳ
▫️ አካባቢህን (environment) አስተካክል
▫️ መንፈስ ቅዱስ ሲወቅስህ ወይም ሲመራህ. . አድምጥ
📍አካልህንና አእምሮህን አበርታ
አሰልጥን ፣ ተንቀሳቀስ ፣ ንቁ ሁን ፣ በአንድ ረገድ የምታሳየው ዲስፕሊን (ሥርዓት) በሌሎችም የሕይወትህ ክፍሎች ላይ ሥርዓትን ይገነባል።
📍በዓላማ ኑር
ጸጋህን (ስጦታህን) ተጠቀም ፣ ተጠቃሚ ብቻ አትሁን... ፈጣሪ (create) ሁን ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆን ሕይወትህ ትርጉም ይኖረዋል።
በጽኑ መቆራኘት (Locking in) ማለት ይህ ነው፦👇
▫️ በቃሉ ውስጥ ጊዜ ማሳለፍ
▫️ ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮችን ማስወገድ
▫️ ዕለታዊ ሥርዓት (Discipline)
▫️ በዓላማ መኖር
ይህ የአንድ ጊዜ ፈተና ሳይሆን የሕይወት ቁርጠኝነት ነው። ምክንያቱም ትኩረትህን ለእግዚአብሔር ስትሰጥ... እርሱ የወደፊት ሕይወትህን ይቀርጻል።
👋በነገር ሁሉ የጌታ ጸጋ ይርዳን 👏
31
9
3
2May 7, 2026 1.6K 8