አላህ ልጆችን ለወላጆች በትክክለኛ እምነትና በመልካም ስነ ምግባር ኮትኩተው እንዲያሳድጉ አደራ ሰጥቷቸዋል፤ ግዴታቸውን እንዲወጡም ደንግጎባቸዋል።
እንዲሁም በወላጆች ላይ ሙከራና ፈተናም አድርጓቸዋል። አላህ ባዘዘው መልኩ (አደራቸውን) ኃላፊነታቸውን ከተወጡ አላህ ዘንድ ታላቅ ምንዳንና ብዙ ሽልማቶችን ሲያገኙ፤ በተቃራኒው ኃላፊነታቸውን ችላ ካሉ ደግሞ በቸልተኝነታቸው ልክ ራሳቸውን ለቅጣት ይዳርጋሉ።
አንዳንድ ዑለማኦች (የኢስላም ሊቃውንት) እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ የቂያማ ዕለት ልጆችን ስለ ወላጆቻቸው ከመጠየቁ በፊት ወላጅን ስለ ልጁ ይጠይቀዋል ፤ ምክንያቱም (አባት) ወላጅ በልጁ ላይ ሐቅ (መብት) እንዳለው ሁሉ ልጅም በወላጁ (አባቱ) ላይ መብት አለውና ነው።"
#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች #ምክር_ለተርቢያ
📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!
💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
