@HidayaTerbiya · 1.3K subscribers
Hidaya Terbiya ሂዳያ ተርቢያ የመልካም ትውልድ ማፍርያ! @HidayaTerbiya
The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.
tg.me/go/HidayaTerbiyaIs this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →
Channel created January 22, 2020per Telegram
We have been tracking it since September 8, 2026
In all that time the channel has changed neither its name, nor its @username, nor its avatar.
We show only what we have seen ourselves.
🔥 ልጆቻችሁ ብዙ ይጣላሉ?… እንዴት ታስታርቃላችሁ? በልጆች መካከል ጭቅጭቅና አለመስማማት የተለመደ ነው። ችግሩ መጣላታቸው ብቻ ሳይሆን እንዴት መስማማትና መፍትሄ መፈለግ እንዳለባቸው አለማወቃቸው ነው። 🌱 የጭቅጭቃቸው ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል? • ቅናት • የትኩረት ፍላጎት • ስሜታቸውን በቃል መግለጽ አለመቻል ⚠️ ችግሩን የሚያባብሱ የወላጅ ስህተቶች፦ • በቁጣ መመለስ • ሳታዳምጡ በፍጥነት መፍረድ • አንዱን ከሌላው ማስበለጥ • ጭቅጭቃቸውን ችላ ማለት 💡 …
🌙 ከመኝታ ጊዜ በፊት ተጠንቀቁ! ልጆቻችን ከመተኛታቸው በፊት ደስተኞችና ደህንነት የሚሰማቸው እንዲሆኑ መርዳት ለስብዕናቸው እጅግ ይጠቅማል። የመኝታ ጊዜን በወቀሳ፣ በዛቻና በቁጣ ከመዝጋት ይልቅ በፍቅር እናጠናቀው። ❌ ከመተኛቱ በፊት አትውቀሱት፤ ✅ አጠገቡ ተቀምጣችሁ አነጋግሩት፣ አስቁት፣ አቅፉት፣ በፍቅር ሳሙት። 🌸 በቀኑ ውስጥ ያደረገውን አንድ ትንሽ መልካም ነገር እንኳን አውስታችሁ አመስግኑት። 📖 ቁርኣን አንብቡለት ወይም አጭርና አስተማሪ ታሪክ ንገሩት።…
🌿 ልጆቻችሁን በምሳሌ አስተምሯቸው! ✨ በልጃችሁ ፊት የተቸገረን ሰው ስትረዱ፣ ስለ ሰደቃ ከምትሰጡት ሺህ ትምህርቶች የበለጠ ተግባራዊ ትምህርት ይወስዳል። ከልጆቻችሁ ፊት ወላጆቻችሁንና ዘመዶቻችሁን ስታከብሩ፣ እነሱም ወላጅንና ዘመድን ማክበርን ይማራሉ። 🗑️ ቆሻሻን በተገቢው ቦታ ስትጥሉ፣ ስለ ንጽህና ከሚሰጡት ብዙ ንግግሮች የበለጠ ውጤታማ ትምህርት ይሆናል። ልጆች ከምንነግራቸውን የበለጠ በሚያዩት ይማራሉ። ⛳️ ተርቢያ ንግግር ብቻ ሳይሆን፤ ምሳሌ መሆን ነው! …
🌱 ልጆቻችሁን ትብብር እንዲለምዱ በጨዋታ አስተምሯቸው! ለልጅዎ የመተባበርን ጥቅም በቃል ብቻ ከመንገር ይልቅ፣ ትብብር የሚያስገኘውን ጥቅም በራሱ እንዲያይ የሚያደርግ (የሚያስተምር) ቀላል ጨዋታ ማጫወት ትችላላችሁ። 🎯 ጨዋታው እንዴት ነው? መጀመሪያ ልጃችሁን መጫወቻዎቹን እንዲያስተካክል ጠይቁት። ሲያስተካክል የሚወስደውን ጊዜ ቁጠሩ (መዝግቡ)። ⏱️ ለምሳሌ 5 ደቂቃ ወሰደ። ከዚያ መጫወቻዎቹን እንደገና በታትኗቸው። በዚህ ጊዜ ግን ብቻውን ሳይሆን አብራችሁ አስተካ…