🔥 ልጆቻችሁ ብዙ ይጣላሉ?… እንዴት ታስታርቃላችሁ?
በልጆች መካከል ጭቅጭቅና አለመስማማት የተለመደ ነው። ችግሩ መጣላታቸው ብቻ ሳይሆን እንዴት መስማማትና መፍትሄ መፈለግ እንዳለባቸው አለማወቃቸው ነው።
🌱 የጭቅጭቃቸው ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል?
• ቅናት
• የትኩረት ፍላጎት
• ስሜታቸውን በቃል መግለጽ አለመቻል
⚠️ ችግሩን የሚያባብሱ የወላጅ ስህተቶች፦
• በቁጣ መመለስ
• ሳታዳምጡ በፍጥነት መፍረድ
• አንዱን ከሌላው ማስበለጥ
• ጭቅጭቃቸውን ችላ ማለት
💡 እንግዲህ ምን እናድርግ?
📌 መጀመሪያ ወላጁ መረጋጋት አለበት።
👂 እያንዳንዱን ልጅ በተራው አዳምጡ።
🗣️ “እሱ እንዲህ አደረገብኝ!” ከማለት በላይ ስሜታቸውን በቃላት እንዲገልጹ አስተምሯቸው።
🚫 አንድ ግልጽ ሕግ አስቀምጡ፦ “መጣላት ሊኖር ይችላል፤ መጉዳት ግን አይቻልም!”
🤝 እርስ በርሳቸው መፍትሄ እንዲፈልጉ እድል ስጧቸው።
🌸 በሰላም ሲግባቡ ግን ያንን መልካም ባህሪ አድንቁ።
📌 አስታውሱ፦ የልጆች አለመስማማት ተፈጥሯዊ ነው፤ ተርቢያ ግን እንዴት በፍቅር፣ በመከባበርና በመግባባት መሰማማት እንዳለባቸው ማስተማር ነው።
🌿 ዛሬ የምታስተምሯቸው የግጭት አፈታት መንገድ፣ ነገ በግንኙነታቸው የሚጠቀሙበት ክህሎት ይሆናል።
#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ሂዳያ
💫 @HidayaTerbiya 💫


















