Halal memory🫀: post #3099 — TG.ME

ስነ-ልቦና፣ ትዳር፣ እና ቢዝነስ እጅግ ውስብስብ እና በየጊዜው እያደጉ ያሉ የዕውቀት ዘርፎች ናቸው። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ለህዝብ ማስተማር ወይም አስተያየት መስጠት የራስን ጠባብ የህይወት ተሞክሮ እንደ አጠቃላይ እውነት (Universal truth) ከማቅረብ የዘለለ መሆን አለበት።
​በዘርፉ በቂ የአካዳሚ ብቃት፣ ሰፊ ንባብ እና ዓለም አቀፋዊ እይታ ሳይኖረው መድረክ ላይ የሚወጣ ሰው፣ እያስተማረ ሳይሆን የራሱን የዕውቀት ማነስ እና መሃይምነት በአደባባይ እያወጀ ነው።
​ በቲክቶክ እና መሰል መድረኮች ላይ የሚንፀባረቁ የ"መንደር ወሬ" እና ያልተብላሉ የተንጠለጠሉ ሀሳቦች፣ የማህበረሰቡን ንቃተ-ህሊና ከማሳደግ ይልቅ ወደ ኋላ ይጎትቱታል።

ዲናዊ ልብስ (እንደ ኒቃብ፣ ሂጃብ ወይም ሌሎች ሃይማኖታዊ መለያዎች) የግለሰብ ምርጫ ብቻ ሳይሆን፣ የትልቅ እሴት እና የሞራል ተምሳሌት ነው። አንድ ሰው ይህንን ገፅታ ተላብሶ አደባባይ ሲወጣ፣ ከራሱ አልፎ የሚወክለው ትልቅ ማንነት አለ።
​ያልበሰሉ፣ በስሜት የተሞሉ እና ከዕውቀት የራቁ ንግግሮችን በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘሩ፣ ተተቹ ግለሰቡ ብቻ ሳይሆን ግለሰቡ የለበሰው ማንነት ጭምር ነው።
​በዘፈቀደ የሚወረወሩ ቃላት እና ተራ የመንደር ወሬዎች የልብሱን እና የገፅታውን ክብር በእጅጉ ያስደፍራሉ። ዕውቀት አልባ ድፍረት የሃይማኖታዊ ማንነትን ክብር ዝቅ ያደርገዋል።


JOIN US: ❯❯𝐇𝐀𝐋𝑨𝐋 _𝚖𝚎𝚖𝚘𝚛𝚢
❤17🍾2😁1
July 31, 2026 2.2K 2