የሚለውን አባባል በዕለት ተዕለት ህይወታችን ስንሰማው እናስተውላለን። ይህ አባባል ከነፍሲያችን፣ ከውስጣዊ ስሜታችን እና ከሸይጧን ጉትጎታ ጋር በሚገባ ስለሚስማማ ብዙዎች ሲያራግቡትና እንደ ትልቅ የጥንካሬ መለኪያ ሲመኩበት ይታያል። እውነታው ግን፣ ይህ እሳቤ ከልዑቁ የኢስላም ስነ-ምግባር (አኽላቅ) ጋር ጭራሽ የማይጣጣም መሆኑ ነው።
የእስልምና ሊቃውንት የሰዎችን ባህሪና ስነ-ምግባር በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይመድቡታል፦
1. አኽላቁን ቲጃሪያ ይህ አይነቱ ባህሪ «መስጠት እና መቀበል» በሚል የጥቅም ህግ ላይ የተመሰረተ ነው። በዚህ መርህ የሚመራ ሰው ስነ-ምግባርን ልክ እንደሚሸጥና እንደሚለወጥ ሸቀጥ ይቆጥረዋል።ለሳቀለት ይስቃል፤ ፊቱን ላጠቆረበት ይኮሳተራል።ለጠየቀው ይጠይቃል፤ ለረሳው ይረሳል።ለሰጠው ይሰጣል፤ ለከለከለው ይከለክላል።
በአጭሩ ይህ የነጋዴ ባህሪ እንጂ፣ ለፈጣሪ ተብሎ የሚደረግ የላቀ ስብዕና አይደለም። የሌሎች ሰዎች ድርጊት የራሱን ምላሽና ፀባይ እንዲወስንበት የሚፈቅድ ደካማ አቋም ነው።
2. አኽላቁን ሙሐመዲያ ይህ ደግሞ ከሰዎች ምላሽ ምንም ሳይጠብቁ፣ ለአላህ (ሱ.ወ) ብለው በንፁህ ልብ መልካምነትን መቸርን ብቻ የሚያውቅ እጅግ የላቀ ባህሪ ነው። ኡለማዎች እውነተኛውን አኽላቅ ሲተረጉሙት እንዲህ ይላሉ፦
"ለከለከለህ ትሰጣለህ፣ ዝምድና ለቆረጠህ ትቀጥላለህ፣ እንዲሁም ለበደለህ ይቅርታ ታደርጋለህ።"
ይህ ከፍ ያለ ስብዕና የውዱ ነብያችን የሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ልዩ መገለጫ ነው። እርሳቸው ክፉ ላደረጉባቸው ሰዎች ጭምር መልካም በመዋል፣ ለገፉአቸው በማዘን የላቀውን ስነ-ምግባር በተግባር አሳይተውናል። እውነተኛው አኽላቅ የሚፈተነው ሰዎች ጥሩ ሲሆኑልን ሳይሆን፣ ሲያጠፉንና ሲበድሉን በምናሳየው ምላሽ ነው።
ጠቅለል ሳደርገው ስለዚህ እኛም ከ"ነጋዴነት" (መስጠትና መቀበል) ባህሪ ወጥተን፣ ሰዎች መልካም ሲሆኑልን ብቻ ሳይሆን ሲርቁንም ሆነ ሲያጠፉን የራሳችንን መርህ ሳንለቅ በነብያዊ ስነ-ምግባር (በአኽላቁን ሙሐመዲያ) ልንታነፅ ይገባል። እውነተኛ ጥንካሬ ያለው የመጣውን በመቀበልና የሄደውን በመሸኘት ሳይሆን፣ ለክፋት በበጎ በመመለስ ውስጥ ነው!
©bekri
JOIN US: ❯❯𝐇𝐀𝐋𝑨𝐋 _𝚖𝚎𝚖𝚘𝚛𝚢
