አዲስ ሪፖርተር - NEWS: post #30855 — TG.ME

የዓለም የልደት ምጣኔ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚያስፈልገው ዝቅተኛ ደረጃ በታች ወደቀ

​በዓለም ታሪክ በጦርነትም ሆነ በወረርሽኝ ወቅት አጋጥሞ የማያውቅ የልደት ምጣኔ ቅናሽ መመዝገቡን የ ZME Science ጥናት ይፋ አደረገ።

የሕዝብ ቁጥርን ሳይቀንስ በተረጋጋ ሁኔታ ለማስቀጠል በአማካይ ለአንዲት ሴት 2.1 – 2.2 ልጅ መውለድ የሚያስፈልግ ቢሆንም፣ አሁን ያለው መረጃ ግን ከዚያ በእጅጉ የወረደ ነው።

​እንደ አዲሱ መረጃ፣ በታይዋን 0.69፣ በደቡብ ኮሪያ 0.8፣ በሲንጋፖር 0.87 እና በቻይና 0.93 ልጅ ብቻ ይወለዳል።

በሩሲያም የልደት ምጣኔው 1.4 አካባቢ ይገኛል።

​በዚሁ ሁኔታ ከቀጠለ የዓለም ሕዝብ ቁጥር በ 2056 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) 9 ቢሊዮን አካባቢ ደርሶ ከፍተኛው ቦታ ላይ ይደርሳል ተብሏል።

ከዚያ በኋላ ግን ዓለም አቀፍ የሰራተኛ እጥረት የሚያጋጥም ሲሆን፣ በጡረታ እና በጤና ስርአቶች ላይ ደግሞ የገንዘብና የግብአት ጫና ከፍተኛ ይሆናል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍5❤3😢2
August 26, 2026 3.1K 5