ኢራን የዶናልድ ትራምፕ ትንሹ ልጅን የሆነውን ባሮን ትራምፕን ለገደለ የ10 ሚሊዮን ዶላር እከፍላለው አለች
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትንሹ ልጅ የሆነውን ባሮን ትራምፕን ለመግደል የታለመ ሴራ የሚያሳይ ቪዲዮ በኢራን መንግስታዊ ቴሌቪዥን ከተሰራጨ በኋላ የአሜሪካ ሚስጥራዊ አገልግሎት (Secret Service) ጉዳዩን ማጣራት ጀምሯል።
በቴሌቪዥን የተሰራጨው ባለ 3 ደቂቃ ቪዲዮ የ20 ዓመቱ ባሮን ትራምፕ እንቅስቃሴ በቅርብ እንደሚከታተል የገለፀ ሲሆን፣ እሱን ለገደለ ሰው የ10 ሚሊዮን ዶላር የጉርሻ ክፍያ እንደተዘጋጀ ገልጿል።
የድርጅቱ ቃል አቀባይ ኔት ሄሪንግ እንደተናገሩት፣ ኤጀንሲው ስለ ቪዲዮው መኖር የሚያውቅ ሲሆን ከደህንነት ጥበቃ ጋር በተያያዘ ስጋት የሚፈጥሩ ማናቸውንም ነገሮች ይመረምራል።
ይህ ማስፈራሪያ የመጣው አሜሪካ እና እስራኤል በየካቲት ወር በኢራን ላይ ጥቃት ካሰነዘሩ በኋላ ሁለቱ ሀገራት በጦርነት ውስጥ ባሉበት ወቅት ነው።
የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻመኔይ በአሜሪካ ጥቃት ከተገደሉ ወዲህ የኢራን መገናኛ ብዙኃን በትራምፕ እና በቤተሰቦቻቸው ላይ ያተኮሩ የተለያዩ የማስፈራሪያ መልእክቶችን ሲያስተላልፉ ቆይተዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

20
11
4August 26, 2026 3.3K 5