አዲስ ሪፖርተር - NEWS: post #30862 — TG.ME

በኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ታሪክ
ከጠቅላላ 600 / 20.67 ብቻ በማስመዝገብ  እጅግ አነጋጋሪ የሆነ ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገበው የ22 አመቱ ተፈታኝ

በዘንድሮው 2018 ዓ/ም በአገር አቀፍ ደረጃ ይፋ የተደረገውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ተከትሎ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ሰፊ አጀንዳ የሆነና በርካታ ተከታታዮችን ያስገረመ የውጤት ዝርዝር ይፋ ሆኗል።

በማኅበራዊ ሚዲያ የመረጃ ገጾች (ጉርሻ ፔጅን ጨምሮ) ከተሰራጩት የውጤት ሰነዶች ማረጋገጥ እንደተቻለው፣ በሶሻል ሳይንስ (Social Science) ዘርፍ ፈተናውን የወሰደው የ22 ዓመት ወንድ ተፈታኝ፣ ከጠቅላላ 600 ነጥብ 20.67 ብቻ በማስመዝገብ በአማካይ 3.45% አስመዝግቧል።

ይህም በኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ ውስጥ በታችኛ ደረጃ ከተመዘገቡት ውጤቶች መካከል እጅግ አነስተኛው እና ያልተለመደው ተብሎ ተጠቅሷል።

ለሕዝብ ይፋ የተደረገው የተፈታኙ የትምህርት ዓይነቶች ውጤት ዝርዝር የሚከተለውን ይመስላል፦

1ኛ. እንግሊዝኛ (English): 8.00

2ኛ. የተፈጥሮ ዝንባሌ ፈተና (Scholastic Aptitude Test): 5.00

3ኛ. ታሪክ (History): 4.00

4ኛ. ጂኦግራፊ (Geography): 2.00

5ኛ. ሒሳብ (Mathematics): 1.67

6ኛ. ኢኮኖሚክስ (Economics): 0.00

የተፈታኙ ግላዊ መብትና  ለማክበር ስሙ ያልተጠቀሰው ይህ ተማሪ ያስመዘገበው እጅግ ዝቅተኛ ውጤት፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችና በትምህርት ባለሙያዎች ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል። ብዙዎች እራሱን ወደ ሚዲያ እንዲወጣ እየጠየቁ ይገኛሉ ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤34🤔7👍3⚡2🙉2👌1🤡1
August 26, 2026 5.3K 47