አዲስ ሪፖርተር - NEWS: post #30865 — TG.ME

ኢዜማ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የተዋቀረውን ኮሚቴን ውድቅ ማድረጉን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ረቡዕ በሰጠው መግለጫ፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ ምክረ ሃሳብ እንዲያዘጋጅ የተሰየመው አስማሚ ኮሚቴ አሰራር የኮሚሽኑን ሕጋዊ ማዕቀፍ የጠበቀ አይደለም ብሏል።

የፓርቲው መሪ አቶ እዮብ መስፍን እንደገለጹት፤ የኮሚቴው አወቃቀርና አካሄድ የኮሚሽኑን ሕግ ያልተከተለ በመሆኑ ፓርቲው አጠቃላይ ሂደቱን ውድቅ በማድረግ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ቅሬታ አቅርቧል።

ኢዜማአክሎም በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ካለው ተቃውሞ በተጨማሪ፤ በምክክሩ ወቅት የቀረቡ 400 ያህል ምክረ ሃሳቦችና የውይይት ቃለ ጉባኤዎች ለሕዝብ ግልጽ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል።"

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍12❤3
August 26, 2026 1.3K