አዲስ ሪፖርተር - NEWS: post #30869 — TG.ME

ውድ ስልክ በህዝብ በጀት ገዝተዋል የተባሉ
3 ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነት ታገዱ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ በእናቶችና ሕፃናት ጤና ፕሮግራም በጀት ውድ ስልክ ተገዝቷል በሚል በማህበራዊ ሚዲያና በመገናኛ ብዙሃን በተሰራጨው መረጃ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል። መንግስት የህዝብን ሀብት በአግባቡ እና ለታለመለት ዓላማ ብቻ መዋሉን ለማረጋገጥ ባደረገው ማጣራት፣ ጉዳዩን በጥልቀት የሚያጣሩ የፍትህ፣ የኦዲት እና የፀረ-ሙስና አካላትን አደራጅቶ ወደ ምርመራ ስራ መግባቱን አስታውቋል።

በጉዳዩ የተጠረጠሩ ሦስት አመራሮችም ከዛሬ ጀምሮ ከኃላፊነታቸው እንዲታገዱ ተደርጓል። የክልሉ መንግስት ማጣራቱ እንደተጠናቀቀ የህዝብን ሀብት ባባከኑ አካላት ላይ የማያዳግም ህጋዊ፣ ፖለቲካዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጾ፣ ህዝቡ የብልሹ አሰራር ጥቆማዎችን በመስጠትና ከጎኑ በመቆም ያደረገውን ተሳትፎ አድንቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
👍17❤11🤣3
August 27, 2026 2.7K 4