በናይጄሪያ የ101 ዓመቷ አያት በአደንዛዥ ዕፅ ንግድ ታሰሩ
በናይጄሪያ ደቡብ ምዕራብ ክፍል በምትገኘው ግዛት ነዋሪ የሆኑ የ101 ዓመቷ ኤስተር ኦጉንማቦ የተባሉ አረጋዊት ማሪዋና (ካናቢስ) ሲሸጡ በመገኘታቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
የናይጄሪያ የዕፅ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ (NDLEA) እንዳስታወቀው፣ አያት ኤስተር በአካባቢው ለሚገኙ ነዋሪዎች በትንሽ በትንሹ የታሸገ 'ስከንክ' የተባለ የማሪዋና አይነት ሲሸጡ ተደርሶባቸዋል።
አረጋዊቷ ለፖሊስ በሰጡት ቃል፤ ቀደም ሲል የነበራቸው የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቃቸው በእሳት ከተቃጠለባቸው በኋላ ገቢ ለማግኘት ሲሉ ወደ እፅ ንግዱ መግባታቸውን ተናግረዋል።
እንደ ኤጀንሲው ገለጻ፣ በሌጎስ የምትኖረው ሴት ልጃቸው በየአራት ቀኑ ዕፁን አዘጋጅታ የምታቀርብላቸው ሲሆን፣ እሷም ለምርመራ በቁጥጥር ስር ውላለች።
የዕፅ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲው ስራ አስፈፃሚ ሞሐመድ ማርዋ አረጋዊቷን በእድሜያቸው ምክንያት በዋስ እንዲፈቱና የምክር አገልግሎት እንዲሰጣቸው አዝዘዋል።
ሆኖም በዋስ መፈታታቸው ከህጋዊ ተጠያቂነት እንደማያድናቸውና ክስ ሊመሰረትባቸው እንደሚችል ተገልጿል ሲል የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ሰሞኑ ዘግበዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

10
5
3
3
2August 26, 2026 3.2K 5