ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ኮሚቴ ሊቀመንበርነትን ተረከበች
ኢትዮጵያ በዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የአፍሪካ ቀጠና ኮሚቴ ሊቀመንበር በመሆን ተመረጠች። የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ሀገሪቱን በመወከል የሊቀመንበርነት ስልጣኑን ከማሊ የጤና እና ማህበራዊ ልማት ሚኒስትር ከኮሎኔል አሳ ባዲያሎ ቱሬ መረከባቸው ተነግሯል።
በ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ጉባኤ ላይ የተረከበው ይህ ኃላፊነት፣ አህጉራዊ የጤና ፖሊሲዎችን በመምራት ረገድ ለኢትዮጵያ ትልቅ አቅም የሚሰጥ ነው ተብሏል።
በዚሁ ጉባኤ የኒጀር የህዝብ ጤና እና ንፅህና ሚኒስትር ዶ/ር ጋርባ ሃኪሚ እንዲሁም የዚምባብዌ የጤና እና ህፃናት እንክብካቤ ሚኒስትር ዶ/ር ዳግላስ ሞምቦሾራ የኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበር በመሆን አጽድቀዋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
9August 26, 2026 2.9K 4

