አዲስ ሪፖርተር - NEWS: post #30861 — TG.ME

የዋጋ ግሽበት በሐምሌ ወር ወደ 15.3 በመቶ ከፍ ማለቱን  የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ!

በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት በሐምሌ ወር ብቻ ወደ 15.3 በመቶ ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ።አገልግሎቱ ባወጣው የወርሃዊ የዋጋ ንረት መረጃ፣ በሐምሌ ወር የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ከባለፈው አመት ጋር ከነበረው 13.7 በመቶ  ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ አድርጓል።  ሰኔ ወር ላይ የነበረው 14.8 በመቶ ነበር።

በዚህ ወር የምግብ ዋጋ ንረት 15.7 በመቶ ሲሆን፣ የምግብ ያልሆኑ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የዋጋ ንረት ደግሞ 14.8 በመቶ ደርሷል ሲል አገልግሎቱ ገልጿል።የዋጋ ንረቱ በ2018 ዓ.ም. መጀመሪያ ወራት ላይ በመቀነስ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ዳግም እየጨመረ የመጣ ሲሆን በመጋቢት ወር የነበረው የዋጋ ንረት ከወራት ዝቅተኛ ደረጃዎች አንዱ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ወራት ግን ጭማሪ ታይቷል።

በተለይም የምግብ ዋጋ ጭማሪ ለአጠቃላይ የዋጋ ንረቱ መጨመር ዋነኛ አስተዋጽዖ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ሲሆን የምግብ ዋጋ ንረት 15.7 በመቶ መድረሱ የዋጋ ጭማሪው በቤተሰቦች የዕለት ተዕለት ወጪ ላይ ጫና መፍጠሩን ያሳያል።

ባለፈው አመት ከነበረው የዋጋ ግሽበት ከ13.7 በመቶ ጀምሮ በዓመቱ መካከል እስከ 9 በመቶ አካባቢ ዝቅ ብሎ ነበር።ይሁን እንጂ ነገር ዳግም በመጨመር በሰኔ 14.8 በመቶ እና በሐምሌ 15.3 በመቶ ደርሷል። በመሆኑም የቅርብ ወራት የዋጋ ንረት አዝማሚያ በኢትዮጵያ የእቃና የአገልግሎት ዋጋ ጭማሪው እንደገና እየተፋጠነ መምጣቱን ያሳያል ሲል የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ገልጿል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
❤8😢3👍1🙉1
August 26, 2026 2.6K 2