በደቡብ ሱዳን ሁለት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ተገደሉ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስቸኳይ ምርመራ ጠየቀ
ትናንት ሰኞ በደቡብ ሱዳን በተፈጸመ የደፈጣ ጥቃት ሁለት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
ሮይተርስ እንደዘገበው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (UNMISS) ባወጣው መግለጫ፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ሰላም አስከባሪዎቹ መደበኛ የተሽከርካሪ ጥበቃ እና ቅኝት በማድረግ ላይ በነበሩበት ወቅት መሆኑን ገልጿል።
በዚሁ ጥቃት አሰቃቂ ድርጊት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን የገለጸው ድርጅቱ፣ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት በፍጥነት ተለይተው ለሕግ እንዲቀርቡ እና አጣዳፊ ምርመራ እንዲደረግ ጥብቅ ጥሪ አቅርቧል።
እንደ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ከሆነ፣ በዚህ ዓመት (2026) ብቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ የነበሩ ዘጠኝ የሰላም አስከባሪዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ደቡብ ሱዳን ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት የሰላም አስከባሪዎች ለከፍተኛ አደጋ እየተጋለጡ ሲሆን፣ ድርጅቱ በአካባቢው ሰላምና ደኅንነት ለማስከበር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

13
7
3August 25, 2026 3.8K 2