" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።
በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
- በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
- ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
- አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

5
2August 25, 2026 4.9K 25