"…መልካም…
"…ሙሉ ሰነዱን አሁንም ደግሜ ደጋግሜ እያነበብኩት ነው። ከትናንት ጀምሮ በህልም ዓለም ውስጥ ያለሁ ያህል እየተሰማኝ ነው ያለሁት። ሰሚ ባይኖርም እኔ ግን እስክሞት ድረስ ከመናፍስቱ ጋር መዋጋቴን አልተውም።
"…ለማንኛውም ከጠዋት ጠዋቱ የእግዚአብሔር ሰላምታ በቀር እጽፍ ዘንድ አስገዳጅ ሁኔታ እስካልተፈጠረ እና እስካልገጠመኝ ድረስ እስከ እሁድ ምሽት የመረጃ ቴሌቭዥን "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" የቀጥታ ሥርጭት የቴሌቭዥን መርሀ ግብሬ ድረስ ምንም መተንፈስ አልፈልግም። ከምር ያደክማል። ማረፍም እፈልጋለሁ።
"…እናንተ ግን በርቱ። መታሰሩ እንዲሁ ባይቀርላችሁም እናንት የአዲስ አበባ ዐማሮች እና ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች እሁድ ከተጠራው የኢዜማ ግንቦት 7 እና ኢህአፓ ብልጽግና የጥቅሴ የቁጩ ሰልፍም ራሳችሁን አርቁ። ለዚሁ የበቀል እርምጃ ለህዳር 30ው ሰልፍ ከትግራይ የህወሓት ደህንነቶች አዲስ አበባ እንዲገቡ መደረጋቸውም እየተነገረ ነው። የመሳይ መኮንን ውትወታ ሰምታችሁ ጉድ እንዳትሆኑ። ምክሬ ነው።
"…መጪው የገና እና የጥምቀት በዓል በድምቀት እንዳይከበር ከኦሮሙማው የወሀቢ እስላሞች እና ከብልፅግናው የፕሮቴስታንት ክፍሎች ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች " በዓላቱ ምነው ባልመጡ" ብለው በመንገሽገሽ በስጋት፣ በጭንቀትና በፍርሃት እንዲያዩት ለማድረግ ሲባል አዳዲስ አስደንጋጭ፣ አሸባሪና አማኞቹን ስጋት ውስጥ የሚከቱ አጀንዳዎች ተፈብርከው የሚቀርቡበት ጊዜ ነውና በተጠንቀቅ እና በንቃት ልንንቀሳቀስም ይገባል። አንድ ቀንም ቢሆን እኔ ግን ሰነዱን በቃሌ ለመያዝ እንደ ውዳሴ ማርያም እያነበነብኩ አረፍ ልበል።
• ዋጋ ከፍላችሁ ሰነዱን ለላካችሁልኝ የኢትዮጵያ አምላክ ብድራቱን ይክፈላችሁ። ሁሉም ነገር የሚጠናቀቀው ግን በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን አሸናፊነት ነው።

14
6
1
1December 9, 2023 21.6K 2