ከስር በምስሉ የሚታየውና በአገዛዙ ፖሊሶች የታሰረው ግለሰብ ብቻውን አዲስ አበባ ከተማ መገናኛ አደባባይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርጓል።
"ዐብይ አሕመድ አምባገነን፣ ሌባ እና አራጅ ነው" የሚል መፈክርም ጽፎ በግልጽ አሳይቷል። ከስልጣን ወርዶ ለፍርድ መቅረብ አለበት ሲልም ጠይቋል። ይህ ጀግና ግለሰብ በአደባባይ ደፍሮ ብቻውን የጠየቀው ጥያቄ የሚሊዮኖች ጥያቄ ነው። ዛሬ እሱ በአደባባይ ያደረገው ነገ ሚሊዮኖች ማድረጋቸው አይቀርም።











