ሴት ልጅን መጠበቅ እና ድጋፍ መስጠት ለእኔ የቅርብ ጊዜ trend ጊዜያዊ አቋም ወይም ለsocial media… — የተሰበሩ ልቦች... — TG.ME

ሴት ልጅን መጠበቅ እና ድጋፍ መስጠት ለእኔ የቅርብ ጊዜ trend ጊዜያዊ አቋም ወይም ለsocial media attention ፍጆታ የሚደረግ show አይደለም ከልጅነቴ ጀምሮ ከቤተሰቤ ከአስተዳደጌ እና ከህሊናዬ አብሮኝ ያደገ በማንኛውም ሁኔታ የማልደራደርበት መሰረታዊ core value እና የመኖሬ አካል ነው። ይሄንንም ቢሆን በዚህ channel ላይ ከማጋራችሁ ይዘቶች ከምከተላቸው መርሆች እና ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዬ መረዳት ትችላላችሁ። በዚህ አጣዳፊ እና ስሜት ቀስቃሽ ርዕስ ላይ ለመናገር በመዘግየቴ im sorry የሚል አጭር statement ከመፖስት ይልቅ በየቀኑ በምሰራቸው ስራዎች በባህሪዬ እና በአቋሜ ለሴቶች ደህንነት ከጎናቸው እንደምቆም በተግባር ማሳየቱ ይበልጥ meaningful እና እውነተኛ እንደሆነ ስለምታመንበት ነው። ማንኛውም ሴት ልጅ ያለ ስጋት በሰላም በነጻነት እና በሙሉ ድፍረት የምትኖርበትን safe environment መፍጠር የሁላችንም responsibility Nው። እኔም ሁልጊዜም ለሴቶች ክብር ደህንነት ድምፅ መሆኔን እቀጥላለሁ! በሴቶች ላይ የሚፈጸም ማንኛውንም ዓይነት አካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ጥቃት ድፍረት በጽኑ እቃወማለሁ!
❤25🔥6
August 18, 2026 1.3K 7 2