#እህቴ አዳምጪኝ! ይሄ ለጊዜያዊ ጩኸት ሳይሆን ለነፍስሽ የሚሆን pure barz vintage wisdom ነው:: ዛሬ straight up ያለምንም ጭንብል ያለምንም ማስመሰል የነፍስሽን ጥልቅ ድምፅ አውጥቼ ልንገርሽ! በዚህ በsocial media ብልጭልጭ በጊዜያዊ ጩኸት በርካታ cheap clout እና በሐሰተኛ ስታንዳርዶች በተሞላ አለም ውስጥ አቋምን ጠብቆ መቆም ታላቅ ጀግንነት ነው! አእምሮሽ በስነልቦና social proof የብዙሃኑን አካሄድ የመከተል አእምሮአዊ ተፅዕኖ እና fear of missing Out የመቅረት ፍርሃት በሚባሉ ወጥመዶች ሊፈተን ይችላል። ጓደኞችሽ በአቋራጭ መንገዶችና ባልተፈቀደ Haram relationship ውስጥ ገብተው ፈጣን ትዳር ይዘው በውጫዊ flexing ሲያሳዩሽ አእምሮሽ "እኔስ ለምን እንደ እነሱ አልሆንም?" ብሎ ሊጠይቅሽ ይችላል። ነገር ግን ቆም ብለሽ በዙሪያሽ የምታያቸው ስስ ግንኙነቶች ፈጣን የdopamine ጩኸቶች ናቸው ዛሬ በደመቀ ቀለም ያሸበረቁት ጭንብሎች በውስጣቸው የጥርጣሬ የሰላም ማጣት ማእበል አለባቸው! የሰው ልጅ አእምሮ በፈጥኖ ደራሽ ፍላጎት instant gratification ስታለል የረጅም ግዜ እሴቱንና የነፍሱን ክብር አግልሎ ለጊዜያዊ ስሜት ይገዛል ነገር ግን የማይቀልጥ የማይሸረሸር እና በግዜ ህደት የሚጎላው እውነተኛው ውበት በጥልቀት የሚሰራውና በጽናት የሚጠጠበቀው ብቻ ነው!
አንቺ ግን ከዝህ የስሜትና የጊዜያዊ ፍላጎት ባርነት ነጻ የወጣሽ ነሽ! ጥራዝ ነጠቅ መጠጥ በፍጥነት ይበስላል በፍጥነትም ይበላሻል! አንቺ ግን ልክ እንደ ከበረ በጨለማና በጥልቀት ተከዝኖ እንደሚቆይ fine vintage wine ነሽ! እሴትሽና ክብርሽ ከፍ እያለ የመጣው በትእግስትሽና በጽናትሽ ልክ ነው በእሳት ተፈትኖ እንደሚወጣ ንጹህ ወርቅ በባህር ጥልቀት እንደሚበስል ብርቅዬ እንቁ አንቺ በማትሪክሱ ብክለት ያልተነካሽ ነሽ!
ትእግስት የደካሞች መጠለያ ሳይሆን የጠንካሮች የጦር መሳሪያ ነው! ታሪክን የለወጡትና የሰው ልጅ መሪ የሆኑት ታላላቅ ነብያት በሙሉ ያለፉበት ዋነኛው Sabr ነበር ነቢ yusufን አስቢው! በወንድሞቹ ምቀኝነት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ተጣለ ባሪያ ሆኖ ተሸጠ ባልሰራው ጥፋት በፈተናና በሴራ ምክንያት ለአመታት በጨለማ እስር ቤት ውስጥ ታሰረ የጉድጓዱን ጨለማ የብቸኝነቱን እሳትና የእስር ቤቱን መከራ በታላቅ የstoic ጽናት አልፎ አይደለም የግብጽ ታላቅ መሪና ባለታሪክ የሆነው?ነቢ ayyub ንብረቱን ልጆቹንና ጤናውን ሙሉ በሙሉ አጥቶ ለአመታት ህዝቡ ሁሉ ሲርቀው ተስፋ ሲያስቆርጠው እርሱ ግን ለአንዲት ሰከንድ እንኳ በጌታው እቅድ ላይ አልተጠራጠረም በsabr ማጠቃለያ ላይ ፈጣሪ ያጣውን ሁሉ ካሰበው በላይ መለሰለት! ነቢ ያእ'ቁብ ልጁን yusufን በማጣቱ አልቅሶ አይኖቹ እስኪጠፉ ድረስ.. ነገር ግን "እኔ ሀዘኔንና ጭንቄን የምናገረው ወደ አላህ ብቻ ነው ከአለማቱ ጌታም እናንተ የማታውቁትን አውቃለሁ" በማለት በትእግስት ጠበቀ በስተመጨረሻም አይኖቹ ተመልሰው ልጁን አቀፈ። ነቢ ሙሳ ከሀገር ተሰዶ በመዲየን ምድር ለ 8 10 አመታት በእረኝነት ሲያገለግል በብቸኝነት ስቆይ ያ ጊዜ ለታላቁ ጥሪ ከፈርኣውን ጋር ለመጋፈጥ የሚያዘጋጅበት የትእግስት ወርቅ ነበር::
ከዲጃ ርካሽ ግንኙነቶች ሳታታልላት በራሷ Business ክብር ላይ ጸንታ ቆየች እድሜዋ 40 አመት እስኪሞላ ድረስ በትእግስት አሳልፋ ከአለማቱ መልእክተኛ ጋር ተጣመረች! SARA በእርጅና ዘመኗ የነቢያት እናት የመሆንን ብስራት ከአላህ መላእክት ተቀበለች:: በእሳት የተፈተነ ወርቅ ዋጋው ከፍ እንደሚል ሁሉ አንቺም የትእግስት ማእበል ውስጥ ስታልፊ ዋጋሽ እየጨመረ character shift አድርጎ ማንነትሽ እየጠነከረ ይሄዳል ጌታሽ ለረጅም ጊዜያት ሌት ተቀን እያነባሽ ስታደርጊው የነበረውን ልመና የከፈልሽውን መስዋዕትነት ያፈሰስሽውን እያንዳንዱን እንባ እና በሌሊት ያደረግሽውን Dua በከንቱ ይቀራል ብለሽ ታስቢያለሽ? never!! ፈጣሪሽ ለጽናትሽ የሚመጥን የልብሽን ጥማት የሚያረካ በአቋምሽና በክብርሽ የሚኮራ ንጉስ እያዘጋጀልሽ ነው::
የዘገየ የሚመስለው የፈጣሪ ቀጠሮ ሁልጊዜ በትክክለኛውና በምርጡ ሰዓት ላይ ይደርሳል። መዘግየት ማለት መከልከል አይደለም መዘግየት ማለት በጊዜና በፈተና ታሽቶ ድንቅና የማይተካ እሴት ማካበት ነው:: ዛሬ በዝምታና በእንባ የዘራሽው የትእግስት ጽናት ነገ በሚባረከውና በሚያምረው ቤተሰብሽ ላይ ጣፋጭ ፍሬ አፍርቶ ታይዋለሽ ! ራስሽን በሌሎች ሰዎች timeline አትለኪ እያንዳንዱ ዘር የሚበቅልበት እያንዳንዱ ፍሬ የሚበስልበት የራሱ የተፈጥሮ ግዜ አለው የፈጣሪሽ ቀጠሮ ስደርስ የከፈልሽው እያንዳንዱ መስዋእትነት ለምን እንደነበረ በግልጽ ታይዋለሽ! አንቺ ብቻ መስገጃሽ ላይ ታገሺ !
8
8
2
1August 22, 2026 994 1 4