Yoo! Bruvv?
Wazzup Bro! ምነው ፊትህ ጠቁሯል ፊጥ ብለሃል? What's the story ምን ተፈጠረ?
ከፍቅረኛዬ ጋር Breakup አደረግን!
Damnnn! በምን ምክንያት? የምን ድንገተኛ መለያየት ነው? ምን ተበላሽቶ ነው?
ያው እሷው ራሷ exit line መረጠች.. «መለያየት ይሻለናል» አለችኝ እኔም በቃሌ ተገኝቼ egoዬን ገትቼ "እሺ ፍላጎትሽን አከብራለሁ" ብዬ ሸኘኋት።
Good move! አለመለመን ትልቅ ወንድማዊ ማንነት ነው ግን ያንተ internal vibe እና ሀሳብ ምንድን ነው?
ውስጤ በቁጭትና በስሜት እሳት እያረረ ነው..
ለመሆኑ ይህን ያህል የሚያቃጥልህና የሚቆጭህ ምኑ ነው?
እኔ የእሷን ክብርና ንፅህና እንደ ወርቅ ጠብቄላት እሷ ግን ልቤን በካራ ሰነጠቀችው ጥፋተኛው እኔው ነኝ.. የፍቅር አጋጣሚዎች በነበሩን ጊዜያት ሁሉ አብረን አልጋ ላይ ሆነን በስሜት ታውረን ወደ sex ልንገባ የምንችልባቸውን ጥልቅ አጋጣሚዎችና መደለያዎችን እኔው ራሴ ገትቼና ተጠንቅቄ የተውኳቸው ነገሮች ነበሩ እሷን በስሜት ጥስቅ አድርጌ አካሏን ለመውሰድ 100% chance እና አጋጣሚ እጄ ላይ እያለ የራሴን ስሜት ገትቼ የተውኩት እኔው እራሴ ነኝ ።
Nahh ለመሆኑ ክብሯንና ንፅህናዋን አስከብረህ በመሸኘትህ ነው የሚቆጭህ? ወይስ አእምሮአቸው corrupt በሆኑ የማይረቡ ጓደኞችህ ፊት "በስሜት አቃጥዬ አካሏን ወሰድኳት ጣልኳት" ብለህ በከንቱ ለመፎከርና flex ለማድረግ ፈልገህ ነበር ?
ያው ጓደኞቼ uncool ነህ ፋራ ነህ እያሉ egoዬን ስለሚነኩት ነው..
What did they say? ምን አወሩብህ?
«እንዴት እስካሁን አካሏን አልተጋራህም? አልጋ ላይ አውጥተህ በስሜት አቃጥለህ አካሏን ሳትወስድ እንዴት ታመልጥሃለች? ለዛኮ ነው የናቀችህ ደግሞ የዘመኑ ሴት physical intimacy chemistry እና የፆታ ግንኙነትን እጅግ በጣም ትፈልጋለች» እያሉ..
Listen to me very carefully bro! ላንተ የማይመጥንና vibeህን የሚያወርድ ዝቅተኛ አስተሳሰብ አትቀበል! አንድ እውነተኛ ወንድ የሚለካው በስሜቱ ላይ ባለው control እንጂ ሴትን በስሜት አታልሎ አልጋ ላይ በመጣልና አካሏን በመበዝበዝ አይደለም! የሁለታችሁን ክብርና ንፅህና መጠበቅህ ላንተ ኩራት እንጂ ውርደት ወይም loser ነህ ማለት አይደለም! ነገ ጧት በስሜት ታውራችሁ "አካሌን በዝብዞ ሕይወቴን አበላሽቶ የጣለኝ አታላይ" ብላ እያለቀሰች ሕይወትህን በቁስልና በእርገማን እንዳታደናቅፈው ታላቅ peace of mind ሰጥተሃታል ክብሯንና ሕይወቷን ከስሜት መነዳት አድነሃል።
በውነቱ ይህንን የተበላሸና ደረጃውን ያልጠበቀ mindset አእምሮዬ ውስጥ የጫኑብኝ ራሳቸው እነዚያ toxic ጓደኞቼ ነበሩ.. በንዴትና በቁጭት ስሜት overreact አድርጌ ነበር ነገር ግን እውነታውን ተቀብያለሁ። Level up የማደርግበትና ትኩረቴን ወደ አላማዬ የምመልስበት ጊዜ አሁን ነው! Thanks a lot!
ምንም ማለት አይደለም! ሁልጊዜም ከጎንህ ነኝ! በበደልና በቁስል ውስጥ አልፈህ ነገ የራስህን ድንቅ መንገድ እንደምትጨርስ አምናለሁ በሚቀጥለው ጊዜ «አገባሁ» ብለህ በደስታና በድል አድራጊነት እንጂ «በታማኝነቴ ተናቅሁ ignore ተደረግኩ» የሚል ተስፋ የቆረጠ ቃል ከአንተ አፍ መስማት አልፈልግም!
13
6August 18, 2026 1.2K 3