ብዙ ሃሳቦች አሉኝ. . . ማንም እንዳያውቃቸው በልቤ ጓዳ የቆለፍኳቸው ብነገሩ ኖሮ ህመሜን የሚያስታግሱ ግን… — የተሰበሩ ልቦች... — TG.ME

ብዙ ሃሳቦች አሉኝ. . .
ማንም እንዳያውቃቸው በልቤ ጓዳ የቆለፍኳቸው
ብነገሩ ኖሮ ህመሜን የሚያስታግሱ ግን ደግሞ እንዳይወጡ ህግ የታገቱ
{​ዝምታ ወርቅ ነው} ይላሉ ሰዎች . .
እኔ ግን ዝምታዬ ውስጥ እየፈረስኩ ነው።
ብናገረው የምወደውን ሰው አጣለሁ ባልናገረው እራሴን አጣዋለሁ።
​በነገሩን ስንት ነገር ይበላሻል ?
ባልተናገርነው ስንት ነገር እኛን ያፈርሰናል ?
በሁለት ጽንፍ መካከል ቆመን የውስጣችንን ጦርነት የምንዋጋ ስንት ሚስኪን ነፍሶች ነን አንደበታችን ዝም ስል ልባችን ግን ጩሀቱን አላቆመም በማለታችን ከማጣት በመቅረታችን መቃጠልን መርጠን የምንኖር ስንት ብዙዎች ነን ! . .
😢19❤6
July 13, 2026 2.7K 3 15