ዛሬ አትመጭም?» «ዛሬ ማርያም ናት አልነካም!» «ነይ እኔም አልነካሽም!» «አንተማ ወንድ አይደለህ እንዴት… — ወግ ብቻ — TG.ME

«ዛሬ አትመጭም?»
«ዛሬ ማርያም ናት አልነካም!»
«ነይ እኔም አልነካሽም!»
«አንተማ ወንድ አይደለህ እንዴት ብሎ ያስችልሀል?»
«ወንድ ልጅ አያስችለውም ያለሽ ማነው?»
«ቢያስችላችሁማ መች ከፍላችሁ ትተኙን ነበር?»

(ዝም ብሎ ትንሽ ማሰብ...ከአባባሏ ላይ ስትህት ማጣት...ልመናውን መቀጠል...)

«ቆይ እኔ ብዙ ቀን ሳልነካ አልመለስኩሽም?»
«እና በራስህ ፍላጎት ነዋ! ቤትህ መጥቼ 'አትንካኝ' ብልህ ግን ለራሴም አያሳምነኝ...አንተም የሌለብህ ሰይጣን መውጣቱ አይቀርም።»
«እእእ እና ያሁኑንን ወር ስራ ብትገቢባት ማሪያም ትቀይምሻለች?»
«በሀይማኖቴ አታሹፍ!»
«አንቺ ነሽ'ኮ እያሾፍሽ ያለሽው። ገላሽን ሽጠሽ እያደርሽ ማሪያምን አልነካም ስትይ አታፍሪም?»
«አትግማማብኝ ስልኩን እንዳልዘጋው!»
«እንዳታስቢው! ዛሬ ካልመጣሽ ማሪያምን አብዳለሁ። እየቀለድኩ አይደለም። ኃላ ጨርቄን ጥዬ ያዩኝ 'ግብዳ ቁ ላ የሌለው እብድ መጣ' እያሉ ከሚዘባበቱብኝ በጊዜ መጥተሽ ተንከባክበሽ ብታስተኝኝ ይሻልሻል።»

(ዝም ብላ ትንሽ ማሰብ...ከአባባሉ ላይ ስጋት ማሽተት...)

«ከደረቅክ ደረቅክ ነዋ...ያለ ልብህ አትሰማም።» (በተሸነፈ ድምፅ)
«እሽ ነይ አሁን ቤቱን ፏ አድርጌያለሁ። የምትወጂውን ኬክ ገዝቻለሁ። ሻወር ጥዬሽ አልገባም ብዬ ፎጣ አገልድሜ ነው የማወራሽ።»
«እሽ መጣሁ። የማሪያም ፀበል ፃዲቅ ልያዝልህ?»
«ግዴለም አንቺ ትበቂኛለሽ።»
«አይባልም»
«እሺ ሌላ ጊዜ ታመጭልኛለሽ የዛሬው ይለፈኝ።»

(ስትመጣ ሻወር ወስዷል...ብቻዋን ገብታ መውሰድ...ከዛ በኃላም የባጥ የቆጡን እያወራት መዞር...ማቀፍ የለም...መሳሳም የለም...ወሬ ብቻ...መዞር ብቻ...)

«በጣም የሚገርመኝ እኮ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? 'አልመጣም' ያልኩህ ቀን እንባ ቀረሽ ልመና ነው የምትለምነኝ። ስመጣ ግን የለመንከኝን ያህል ፈጥነህ ልትነካኝ አትሞክርም። አንዳንዴማ ከነጭራሹም ሳትነካ ትመልሰኛለህ። ከዚህ የምታገኘው እርካታ ምንድን ነው? ማለቴ ይሔ እንዴት ያለ የወሲብ አይነት ነው? የወሲብ አይነት ከሆነስ ባህላችን ይፈቅደዋል ወይ? ሂሂ»
«ይሔ ያስቃል።» (ሳይስቅ)
«የምሬን ነው። ያስፈራኛል ይሔ አመልህ።»
«በጣም የምትወጂው ነገር ምንድን ነው ማርቲዬ?»
«ኬክ ነዋ እያወቅከው»
«እሺ ቆይ ያልበላሻት ትንሽዬ ኬክ ፍሪጁ ውስጥ ብትኖር ሳትበያት ስለሌላ ነገር ማሰብ ትችያለሽ?»
«እንዴት ብዬ?»

«የኔም ነገር እንደዛው ነው። በእረፍት ቀኔ አንቺ ከሌለሽ ይጨንቀኛል። ሀሳብ ብቻውን አገኘሁት ብሎ ተመቻችቶ ይተኛብኛል። አንቺ ቤት ካለሽ ግን ስሌላ ነገር ማሰብ አልችልም። ሽፍደቴ ጣልቃ እየገባ ጭንቀቴን ሁሉ ይበትነዋል።»

«ኦውውውው የምር እኔ ኬክ የምወደውን ያህል ትወደኛለህ ማለት ነው? እንባዬ መጣ ማሪያምን!»
«ኧረ ብዙም ደስ አይበልሽ ላንቺ አይደለም ለገላሽ ነው እንደዛ ያልኩት።»
«ሒድ! ምኑ ግማታም ነው በማሪያም? ሸ ርሙጣ!»
«ምኗ ነሽ አንቺስ? መሐንዲስ!»
«ማሾፍህ ነው?»
«በሙያሽ ሰደብሽኝ በሙያዬ ሰደብኩሽ።»
«ሰው እንዴት ሰውን 'መሐንዲስ' ብሎ ይሳደባል? መማታት እየተቻለ?»
«ሃሃ ቆንጆ ተጫወትሽ አሁን...»
«ግን...ግን»
«እ?»
«ምን አይነት ሀሳብ ቢኖርብህ ነው ይሔን ያህል ለመሸሽ መላ የምትፈልገው?»
«ምንም!...ማለቴ እንዲህ ነው ተብሎ የሚነገሩ አይደሉም። ዝምብለው ተራ ነገሮች ናቸው። ብቻ አዕምሮዬ ስራ ፈትቶ አያግኙት!»
«አልገባኝም?»
«ለማስረዳትም የሚመቹ አይደሉም።»
«አንቺ አይገባሽም ደደብ ነሽ የሚል ንቀት ባይኖርብህ የተወሰነ ልታስረዳኝ ትሞክር ነበር።»

«ተንኮለኛ ነሽ እንደው። እንዴት ብዬ ልንገርሽ ማርቲዬ? አሁን ባለፈው አንቺ የቀረሽ ቀን እዚህ መታጠፊያዋ ጋ የጀበና ቡና የምትሸጠው ሳቂታዋ ልጅ የለችም? ድንገት ሀሳብ ውስጥ ገብታ ቡና ደፋችብኝ። ተናድጄ 'አቦ ይድፋሽ' ብላት 'ኧረ አሜሜሜን' አለችኝ በተማረረ ድምፅ። ደብሮኝ ዋለ። የባለፈው ባለፈው ደሞ አውሮፓ ያለችው የጎረቤቴን ልጅ እያወራኋት 'መቼ ነው የምትመጭው?' ስላት 'ሀብታም ባል ሳገባ' አለችኝ እየሳቀች። እኔ ግን ሳለቅስ አመሸሁ። የባለፈው ባለፈው ባ...»

«ኧረ በቃህ! አንተ ዝም ካልኩህ 'መብራት በርቶባቸው መኪኖቹ ሲቆሙ አለቀስኩ' ትለኛለህ። ምኑ ንፍሮ ነው በማሪያም!»
«ይቅርብሽ ብዬ ነበር እኮ እኔም...ራስሽ ነሽ...»
«ስቀልድ ነው ተረድቼሀለሁ። ግን የጠበኩት ከድሮ ሚስትህ ጋ የተያያዘ ነገር ነበር!»

(ቀጥ ብሎ እይት...ስታዬው አይኑን ስብር...)

«ምን ሰምተሽ ነው?»
«ምንም»
«ባክሽ ታስታውቂያለሽ የሰማሽው ነገር እንዳለ!»
(መስኮት መስኮት እያዬ ትክዝ..)
«እሺ! ግን አይደብርህማ ቢነሳ?»
«አትቅለስለሽ! ሁሌ አይደል እንዴ ልታነሽብኝ የምትሞክሪው? እኔ ሆን ብዬ ርዕስ ስለምቀይርብሽ እንጂ! በይ አውሪውና ይውጣልሽ!!»
«ኧረ ማሪያምን እኔ ለዛ አይደለም። ከፈለግክ አለማውራት እንችላለን። እንዲደብርህ አልፈልግም።»

«እንደሌላው ሰው ዙሪያጥምጥም አትሒጂ እንጣላለን!»

«እሺ! እንትን? ማለቴ ሰራተኛዋ ቆንጆ ነበረች?« (እንደመሳቅ እያለች)
«አልነበረችም። አፈር ነች!»
«እና ለምን? ማለቴ?..»
«ለምንም! በቂ ምክኒያት የለኝም። ሚስቴ ፊልድ ሔደች። በዕረፍት ቀኔ ብቻዬን ሆንኩ። ሀሳብ በዛብኝ። ከሀሳብ ለመውጣት ቁ ላዬን የማስቀምጥበት ጉድጓድ ፈለግኩ። ሰራተኛችንን አገኘሁ። ወጣሁባት። ሚስቴ ያዘችኝ። ተፋታን። ይሔው ቀልዬ እኖራለሁ አንገቴን ደፍቼ። እ? አሁንስ ደስ አለሽ? ወሬኛ!!»
«ኧረ ተው እንደሱ አትበል በማሪያም! ሁሉም ሰው ይሳሳታል'ኮ!»
«ሃሃ ይልቅ ነይና እቀፊኝ...ደስ ይበልሽ...መጨነቅ ጀመርኩ።»

(ተነስታ እቅፍ...አናቱን ወስዳ ጡቶቿ ውስጥ ሽጉጥ...እሱ ተጠጋችኝ ብሎ ሰውነቷን መሳም...እሷ ጆሮው ቀረበኝ ብላ ማንሾካሾክ...)
«ያለ ነው። ያጋጥማል። ሁሉም ይጥላህ። ብቻ አንተ ራስህን አትጥላ። ሁሉም ይናቅህ። ብቻ አንተ ራስህን አትናቅ። ሲያስመስሉ ነው'ጂ ተሳስቶ የማያውቅ የለም። ስለማይነግሩን ነው'ጂ ያልወደቀም የለም!!»

«መውደቄ መች ከበደኝና ማርቲዬ! የጣለኝ ፈተና ትንሽነት እኮ ነው እንዲህ የሚያደርገኝ። እንደ ዝንብ ቀልሎ ያልተገኘን የሸረሪት ድር ይጥለዋል?...
...ይልቅ እሱን ተይውና ዝምብለሽ እቀፊኝ። ጥብቅ አድርገሽ ያዥኝ። እፉዬ ገላ ነኝ...ከተውሽኝ ንፋስ ይወስደኛል...»

(እስኪጨራመት ድረስ አጥብቃ እቅፍፍፍ...በጣቶቿ መሀል ሾልኮ እንዳይንሳፈፍ!)

፨፨፨፨፨

By Michel Azmeraw

@wegoch
@wegoch
@paappii
❤84😁15
July 21, 2026 7.7K 28