ከክርስትና በፊት የነበረው አረማዊው ዓለም (pagan world) ድሆች ፣ ሕሙማን እና አካል ጉዳተኞች በአማልክቱ የተረገሙ እንደሆኑና ርኅራኄ እንደማይገባቸው ያምን ነበር። ለእነዚህ የተገለሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች መራራት ለአረማዊው ዐለም እንግዳ የሆነ፣ የክርስትና ግን መሠረታዊ ተፈጥሮ ነበር። ክርስቲያኖችም ከአረማውያኑ የሚለዩበት ልዩ መታወቂያቸው ይህ ለተቸገሩትና ልዩ ልዩ ደዌ ለጸናባቸው ሰዎች የሚያሳዩት ፍቅር ርኅራኄና እንክብካቤ ነበር። በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን ለነበሩ ክርስቲያኖች ምጽዋት እንደ አማራጭ በጎ ስራ (virtue) የሚደረግ አልነበረም። ይልቁንም ክርስቲያን ያደረጋቸው መሠረታዊ ማንነታቸው እንጂ። በዛሬው ቆይታችን ይህንን የጥንቷ ቤተክርስቲያን ስለነዳያን የነበራትን አቢዮታዊ አቋም ፣ ዛሬ ካለው መረዳትና ልምምድ ጋር በስፋት ለማነጻጸር ሞክረናል። መልካም ቆይታ።
https://youtu.be/cy9mYo1cFw0?si=3FKQyHXn4yO_Nnvj