የአምላክ ፊት በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 75፥23 ወደ ጌታቸው ተመልካቾች… — ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics" — TG.ME

የአምላክ ፊት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

75፥23 ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ

"ሲፋህ" صِفَة ማለት "ባሕሪ"Attribute" ማለት ነው፥ የአሏህ ሲፋህ "ሲፋህ ዛቲያህ" صِفَة ذَاتِيَّة እና "ሲፋህ ፊዕሊያህ" صِفَة فِعْلِيَّة ተብሎ ለሁለት ይመደባል።
"ሲፋህ ዛቲያህ" صِفَة ذَاتِيَّة ማለት "የምንነት ባሕሪ"Passive Attribute" ማለት ሲሆን የአሏህ ሕያውነት፣ ዕውቀት፣ ችሎታ፣ ጥበብ፣ ኃይል፣ ዓይን፣ እጅ፣ እግር፣ ፊት ወዘተ "ሲፋህ ዛቲያህ" صِفَة ذَاتِيَّة ነው።
"ሲፋህ ፊዕሊያህ" صِفَة فِعْلِيَّة ማለት "የድርጊት ባሕሪ"Active Attribute" ማለት ሲሆን የአሏህ ፈጣሪነት፣ ፍርድ፣ ይቅርባይነት፣ ከዐርሽ በላይ የበላይነት ወዘተ "ሲፋህ ፊዕሊያህ" صِفَة فِعْلِيَّة ነው።

"ሲፋህ ዛቲያህ" صِفَة ذَاتِيَّة እራሱ "ሲፋህ መዕነዊያህ" صِفَة مَعْنَوِيَّة እና "ሲፋህ ኸበሪያህ" صِفَة خَبَرِيَّة ተብሎ ለሁለት ይመደባል።
"ሲፋህ መዕነዊያህ" صِفَة مَعْنَوِيَّة ማለት "ትርጉማዊ ባሕሪ"Semantic Attribute" ማለት ሲሆን የአሏህ ሕያውነት፣ ዕውቀት፣ ችሎታ፣ ጥበብ፣ ኃይል ወዘተ በዐቅል የምንረዳቸው "ሲፋህ መዕነዊያህ" صِفَة مَعْنَوِيَّة ወይም "ሲፋህ ዐቅሊያህ" صِفَة عَقْلِيَّة ነው።
"ሲፋህ ኸበሪያህ" صِفَة خَبَرِيَّة ማለት "አዋጃዊ ባሕሪ"Informative Attribute" ማለት ሲሆን የአሏህ ዓይን፣ እጅ፣ እግር፣ ፊት ወዘተ በነቅል የምንረዳቸው "ሲፋህ ኸበሪያህ" صِفَة خَبَرِيَّة ወይም "ሲፋህ ነቅሊያህ" صِفَة نَقْلِيَّة ነው።

ይህንን ከተረዳን ዘንዳ "ወጅህ" وَجْه ማለት "ፊት"Face" ማለት ሲሆን የአሏህ ፊት ሲፋህ ዛቲያህ፣ ሲፋህ ኸበሪያህ፣ ሲፋህ ነቅሊያህ ነው። የአምላካችን የአሏህን ፊት የፍጡራን ዓይኖች አያካብቡትም፥ አሏህ ረቂቅ ነው፦
6፥103 ዓይኖች አያካብቡትም፡፡ እርሱም ዓይኖችን ያካብባል፡፡ እርሱ ረቂቁ ውስጠ ዐዋቂው ነው፡፡ لَّا تُدْرِكُهُ الْأَبْصَارُ وَهُوَ يُدْرِكُ الْأَبْصَارَ ۖ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ

"አል-ለጢፍ" اللَّطِيف ማለት "ረቂቁ" ማለት ሲሆን የአሏህ ግርዶ ብርሃን ነው፥ ግርዶሹን ቢገልጠው "ፊቱ" ያገኘውን ነገር ሁሉ ያቃጥላል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 201
አቡ ሙሣ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “አሏህ አይተኛም፥ እርሱ መተኛት አይገባውም። እርሱ ሚዛኖችን ዝቅ ያረጋል ያነሳልም፥ የእርሱ ግርዶ ብርሃን ነው። ግርዶሹን ቢገልጠው "ፊቱ" ያገኘውን ነገር ሁሉ ያቃጥላል"። عَنْ أَبِي مُوسَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ " إِنَّ اللَّهَ لاَ يَنَامُ وَلاَ يَنْبَغِي لَهُ أَنْ يَنَامَ يَخْفِضُ الْقِسْطَ وَيَرْفَعُهُ حِجَابُهُ النُّورُ لَوْ كَشَفَهَا لأَحْرَقَتْ سُبُحَاتُ وَجْهِهِ كُلَّ شَىْءٍ أَدْرَكَهُ بَصَرُهُ "

ነገር ግን በፍርድ ቀን አማንያን አምላካችን አሏህን ተመልካቾች ናቸው፥ በተቃራኒው ከሓዲያን አሏህን ከማየት ተጋራጆች ናቸው፦
75፥23 ወደ ጌታቸው ተመልካቾች ናቸው፡፡ إِلَىٰ رَبِّهَا نَاظِرَةٌ
84፥15 ይከልከሉ! እነርሱ በዚያ ቀን ከጌታቸው ማየት ተጋራጆች ናቸው፡፡ كَلَّا إِنَّهُمْ عَن رَّبِّهِمْ يَوْمَئِذٍ لَّمَحْجُوبُونَ

የአሏህ ግርዶ ብርሃን ነው፥ አማንያን በጀናህ ውስጥ ተጨማሪ የሚያገኙት መንፈሳዊ ጸጋ የአሏህ ፊት መመልከት ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 1 ሐዲስ 354
ሱሐይብ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እነዚያ የጀናህ ባለቤቶች ጀነናህ በሚገቡ ጊዜ የተከበረው እና ከፍ ያለው አሏህ፦ “ጭማሪ እንድሰጣችሁ ትፍልጋላችሁን? ብሎ ይጠይቃቸዋል፥ እነርሱም፦ ፊታችንን አላበራህምን? ወደ ጀናህ አላስገባከንምን? ከእሳትስ አላዳንከንምን? ይላሉ፥ ከዚያ እርሱ ግርዶሹን ያነሳል፥ እርሱ ለእነርሱ የወደደው አሸናፊው እና ክብራማ የሆነውን ከጌታቸውን "ፊት" በስተቀር ለእነርሱ ምንም ነገር በእነርሱ ዘንድ የለም"። عَنْ صُهَيْبٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ إِذَا دَخَلَ أَهْلُ الْجَنَّةِ الْجَنَّةَ - قَالَ - يَقُولُ اللَّهُ تَبَارَكَ وَتَعَالَى تُرِيدُونَ شَيْئًا أَزِيدُكُمْ فَيَقُولُونَ أَلَمْ تُبَيِّضْ وُجُوهَنَا أَلَمْ تُدْخِلْنَا الْجَنَّةَ وَتُنَجِّنَا مِنَ النَّارِ - قَالَ - فَيَكْشِفُ الْحِجَابَ فَمَا أُعْطُوا شَيْئًا أَحَبَّ إِلَيْهِمْ مِنَ النَّظَرِ إِلَى رَبِّهِمْ عَزَّ وَجَلَّ ‏"
August 24, 2026 9.4K 3 24