👇👇👇👇
ፀሎት ስጠኝ
በነጭ አሸብርቄ በረዶ መስዬ
ነጠላ አደግድጌ ዳዊትም አዝዬ
ከደጅህ ብመጣም የምለው ስላጣሁ
ምንም ሳልጠይቅህ እንደሄድኩት መጣሁ
ያው ከነሸክሜ
ከሀጥያት ጭንቀቴ ምንም ሳላወጋ'
የሆዴን ሳልነግርህ ቃላት ሳልዘረጋ
ላንተ የማቀርበው የምለው ስላጣሁ
ምንም ሳልል ሄጄ ምንም ሳልል ወጣሁ
ተደጋገመብኝ ይሄ ፀሎት ማጣት
እንደ በድን ሄደው እንደ በድን መምጣት
ከፊትህ የሚቀርብ ቃላት ስላቃተኝ
ለኔ የሚገባ እግዜር ፀሎት ስጠኝ።
2August 31, 2026 92 1 1