ዘሰንበተ ክርስቲያን ዮሐንስ 6:41-ፍጻሜ አይሁድም ስለ እርሱ አንጐራጐሩ “ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ… — ፀዊረ መስቀል — TG.ME

ዘሰንበተ ክርስቲያን
         ዮሐንስ 6:41-ፍጻሜ


    አይሁድም ስለ እርሱ አንጐራጐሩ “ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ” ብሎአቸዋልና። “እኛ አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? እንግዲህ እንዴት ከሰማይ ወረድሁ  ይለናል?” አሉ። "ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እርስ በርሳችሁ አታንጐራጕሩ። የላከኝ አብ ካልሳበው በቀር ወደ እኔ መምጣትን የሚችል የለም፤ እኔም በመጨረሻዪቱ ቀን አስነሣዋለሁ። ሁሉም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተማሩ ይሆናሉ” ተብሎ በነቢያት መጽሐፍ ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአባቴ የሰማ ሁሉ ተምሮ ወደ እኔ ይመጣል። "ከእግዚአብሔር ከሆነው በቀር አብን ያየው ማንም የለም፤ እርሱም አብን አየው። እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው። የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። "አባቶቻችሁስ በምድረ በዳ መና በሉ፥ ሞቱም። 'ከእርሱ የበላ ሁሉ እንዳይሞት ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው።

“ከሰማይ የወረደ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ከዚህ እንጀራ የሚበላ ለዘለዓለም ይኖራል፤ ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው ይህ እንጀራ ሥጋዬ ነው”

"አይሁድም፥ “ይህ እንበላ ዘንድ ሥጋውን ሊሰጠን እንዴት ይችላል?” ብለው እርስ በርሳቸው ተከራከሩ። “ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ፥ ደሙንም ካልጠጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ፥ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ እኔም በኋለኛዪቱ ቀን አነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል ነውና፤ ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና። ሥጋዬን የሚበላ፥ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ። "የላከኝ አብ ሕያው እንደ ሆነ፥ እኔም ስለ አብ ሕያው ነኝ፤ ሥጋዬንም የሚበላ እርሱ ደግሞ ስለ እኔ ሕያው ሆኖ ይኖራል። *ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው አባቶቻችሁ በልተውት እንደሞቱበት ያለ መና አይደለም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ግን ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ይኖራል።” "በቅፍርናሆምም በምኵራብ ሲያስተምራቸው ይህን ተናገረ፤

ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎቹ ይህን ሰምተው፥ “ይህ ነገር የሚያስጨንቅ ነው፤ ማንስ ሊሰማው ይችላል?” አሉ። ጌታችን ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ነገር እንደ አንጐራጐሩ በልቡ ዐወቀባቸውና እንዲህ አላቸው፥ “ይህ ያሰናክላችኋልን? እንግዲህ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበረበት ሲያርግ ብታዩት እንዴት ይሆን? ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አንዳች አይጠቅምም፤ ይህም እኔ የምነግራችሁ ቃል መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው። "ነገር ግን ከእናንተ ውስጥ የማያምኑ አሉ” ጌታችን ኢየሱስ ከጥንት ጀምሮ የማያምኑበት እነማን እንደ ሆኑ፥ የሚያሲዘውም ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበርና። እንዲህም አላቸው፥ “ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ከአብ ካልተሰጠው በቀር ወደ እኔ መምጣት የሚቻለው የለም።”

"ስለዚህም ከደቀ መዛሙርቱ ወደ ኋላቸው የተመለሱ ብዙዎች ናቸው፤ ከዚያም ወዲህ አብረውት አልሄዱም። ጌታችን ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን፥ “እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትሻላችሁን?” አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “አቤቱ፥ የዘለዓለም የሕይወት ቃል እያለህ ወደ ማን እንሄዳለን? እኛስ የሕያው፤ እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አንተ እንደ ሆንህ አምነናል፤ አውቀናልም።” “ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “እኔ እናንተን ዐሥራ ሁለታችሁን መርጫችሁ የለምን? ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ሰይጣን ነው።” “ይህንም ስለ ስምዖን ልጅ ስለ አስቆሮታዊው ይሁዳ ተናገረ፤ እርሱ ያሲዘው ዘንድ አለውና፤ እርሱም ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ነበር......


ዕብራውያን 3:1-ፍጻሜ
ያዕቆብ 5:1-12
ሐዋ፡ሥራ 22:1-22


👉ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ

ምስባክ
         መዝ· 144 : 15-16


ዐይነ ኵሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ

አንተ ትሁቦሙ ሲሳዮሙ በጊዜሁ

ትሰፍሕ የማነከ ወታጸግብ ለኵሉ እንስሳ ዘበሥርዓትከ

ትርጉም


የሰው ሁሉ ዐይን አንተን ተስፋ ያረጋል

አንተ ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ

ቀኝ እጅህን ትዘረጋለህ በሥርዐትህ ለሚኖሩ እንስሳ ሁሉ ታጠግባለሀሰ
August 29, 2026 115