25/12/2018 የዕለቱ የወንጌል ክፍል ማቴዎስ 3:7-13 ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ… — ፀዊረ መስቀል — TG.ME

25/12/2018
   የዕለቱ የወንጌል ክፍል
          ማቴዎስ 3:7-13


    ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው፦ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ? እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ በልባችሁም፦ አብርሃም አባት አለን እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል። አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤ መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል......

ኤፌሶን 6:10-19
1 ጴጥሮስ 3:1-11
ሐዋ.ሥራ 12:12-20



ምስባክ
       መዝሙር 38:7-8


ወይእዜኒ መኑ ተስፋየ አኮኑ እግዚአብሔር

ወትዕግሥትየኒ እምኀቤከ ውእቱ

ወእምኵሉ ኃጢአትየ አድኀንከኒ

ትርጉም


አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን?

ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።

ከኃጢአቴ ሁሉ አዳንከኝ፥
August 30, 2026 81 1