ህይወትን በጥበብ: post #1433 — TG.ME

አንድ ሬስቶራንት ውስጥ ገብቼ ብርዱን ምቋቋምበት ትኩስ ነገር አዝዤ እንደተቀመጥኩ፡ አንድ በጣም ጥሩ የለበሰ የሚያምር ቁመት ያለው ሰውዬ በእጁ ቦርሳ ይዞ ወደ ውስጥ ገባ፡ ወዲያው አንዲት ሴት ተከትላው ገብታ ወደእርሱ በመሄድ... "ባሌ ሞቷል ልጆቼን የማበላቸው ነገር የለኝም" ..... ሰውየው ምንም ሳይዘገይ ቦርሳውን ከፍቶ አይኔ እያየ 50ሺ ብር ቆጥሮ ሰጣት፤ እኔም በውስጤ WOW በጣም ጥሩ ሰው ነው አልኩኝ፡ ከትንሽ ደቂቃዎች በኋላ አንድ ወጣት መጣ እያቃሰተና እያለቀሰ፦ ወላጆቼ ሞተውብኛል "40ሺህ ብር ስጠኝ የራሴን ቢዝነስ መስራት እፈልጋለው" ሰውየው ያለ ምንም መዘግየት ቦርሳውን አውጥቶ ቼክ ፃፈለት...እኔም በውስጤ እልልልልልልል ይሄን ሰውዬ ፈጣሪ ለእኔ ነው የላከው! ብዬ አመንኩ።

በደንብ ለማልቀስ እንዲያግዘኝ ብዬ የመጣልኝን ትኩስ ሻይ 🥃 ወደ ሆዴ ልኬ በሩጫ🏃‍♀️ ሰውዬው እግር ስር ወድቄ ሱሪውን👖 በእጄ ይዤ እያለቀስኩ😭 "ወንድሜ 4 ልጆች አሉኝ ስራ የለኝም ባሌ ጥሎኝ ጠፍቷል፡ የራሴን ቢዝነስ የምጀምርበት 300ሺህ ብር ስጠኝ"🙏… ሃሃሃሃሃሃሃ 🤣 ውጪ ያሉ ሰዎች ሳቅ🤣 ነበረ ሰውዬውም Cut...Cut...Cut ....አላቸውና Sorry Sister ፊልም ቀረፃ ላይ ነበርን.... ከተደፋሽበት ተነሺ!
.
አቤት ውርደት😹🙊
🙉18😁17❤5🥰1