ህይወትን በጥበብ: post #1411 — TG.ME

ብዙ ሙድ የሚይዙ ሰዎች አጋጥመውህ ሊያቅ ይችላል እመነኝ እንደራስህ አእምሮ ሙድ የሚይዝብህ ነገር ግን ከየትም የለም💯የናንተም ገጠመኝ ካለ comment አድርጉ

፦ለምሳሌ👇

አብዛኛው በሚባል ደረጃ የሚያጋጥመው ነገር ማታ ወደ ክፍልህ ልተኛ ስትሄድ በር ዘግተህ አልጋ ላይ እንደወጣህ በሩ አልዘጋህም ብሎ ያወጫብርሃል። ሽንት ልትሸና ስታስብ ባትሸናስ ምን ትሆናለህ ይለሃል ከዛም ትንሽ ቆይቶ በተወደደ ኩላሊት አትቀልድ እንጂ ሰውዬ ተነስና ሽና ይለሃል🙄

በማይሆን ቦታ የማይሆን ነገር ያስታውስሃል ለቅሶ ቤት ውስጥ ሆነህ ድንገት በልጅነትህ ያደረካቸውን ተንኮሎች ወይንም የሚያስቅ ትውስታችን ያመጣብሃል አንተ በመሃል ላለመሳቅና ለመኮሳተር በምታደርጋቸው ድርጊቶች ለመጨለል ጫፍ ትደርሳለህ ነው የምልህ አባቴ🤣

Library ተመስጠህ እያነበብክ ሁሉም ሰው ፀጥ ባለበት ሰዓት ልጮህ ነው ብሎ ያስፈራራሃል😔

ሌላው ብር ቆጥረህ እስክትጨርስ ድርስ ይጠብቅና ደግመህ ቁጠረው ተሳስተሃል ይለሃል😞

አሁን ከራሳችን በላይ ሙድ የሚይዝብን አካል እንደለለ ነው የተረዳሁት😁
🤣13👏7😁3❤2