ህይወትን በጥበብ: post #1408 — TG.ME

❤️❤️👌👌እጅግ አስተማሪ ነው

አንድ የ78 ዓመት አባት እራሳቸውን ስተው ወደሆስፒታል ይወሰዳሉ ። ለ24 ሰዓት የሚያቆያቸው የመተንፈሻ ኦክስጅን ተሰጣቸው ። ከጥቂት ግዜ በኃላ ተሻላቸውና ዶክተሩ የተጠቀሙበትን ሂሳብ የ500 ዶላር ደረሰኝ ሰጣቸው ። እኝህ አባትም የተሰጣቸውን ደረሰኝ በተመለከቱ ግዜ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ። ዶክተሩም ስለ ገንዘቡ ማልቀስ አይገባዎትም በአንድ ግዜም ባይሆን ቀስ እያሉ መክፈል እንደሚችሉ ነገራቸው ። ሆኖም እኝህ አባት " እኔ የማለቅሰው ስለዚህ ገንዘብ አደለም ገንዘቡን በሙሉ የመክፈል አቅም አለኝ ፤  የማለቅሰው 24 ሰኣት ለተነፈስኩበት ኦክስጅን 500 ዶላር ልከፍል በመሆኑ ነው ፤ ነገር ግን ላለፋት 78 አመታት የፈጣሪን ንፁ አየር በነፃ ስተነፍስ ኖሬያለው ለእነዚ ሁሉ ግዜያት መክፈል ቢኖርብኝ ምን ያህል የፈጣሪ እዳ እንዳለብኝ መገመት ትችላለህ ?? " በማለት መለሱለት

ከተመቻቹ like and share🙏 join us @tibeb145 @tibeb145
❤18👍2🥰2