የፈጠራና ክህሎት ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎች በወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዕከላት እና በወራቤ ዩንቨርሲቲ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ስልጠና እየወሰዱ መሆኑ ተገለፀ!
ተማሪዎቹ የክረምት ዕረፍት ጊዜያቸውን በመጠቀም በወራቤ ከተማ ስልጠና ማዕከላትና በወራቤ ዩንቨርሲቲ የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የወራቤ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ገለፀ።
በዛሬው እለትም የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች ሰልጣኝ ተማሪዎችን የጎበኙ ሲሆን በስፔስ ሳይንስ ዘርፍ እየተማሩ ያሉትን ትምህርትና የስልጠና ሂደት ተመልክተዋል።
ተማሪዎቹም በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና በተግባር እየሰሯቸው ያሉትን ስራዎች አስረድተዋል።
በማዕከላቱ እየተሰጠ ባለው ስልጠና፣ ተማሪዎች ስለ ስፔስ ሳይንስና የህዋ ቴክኖሎጂ መሰረታዊ እውቀት ከማግኘታቸው በተጨማሪ የፈጠራና የምርምር አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ ዕድል የሚፈጥር መሆኑም ተገልጿል ።
የከተማው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው፣ ተማሪዎች የክረምት ዕረፍታቸውን በእውቀት ማዳበሪያ ስልጠናዎች እንዲያሳልፉ መደረጉ ለወደፊቱ የሀገሪቱን የሳይንስና የቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ ጠቃሚ ነው።
በጉብኝቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሙህዲን ሁሴን፣ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ጀሚለ ሁሴን፣ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሹክራላ አወል፣ የወራቤ ከተማ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መሐመድ ባርሰባ እና ሌሎች የዘርፉ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል ።

























