በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች
👉ዘንድሮ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 12 ነጥብ 8 በመቶ ወይም 70 ሺህ 544 ተማሪዎች የማለፊያ ወጤት አምጥተዋል፡፡
👉በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛው ውጤት 591.6 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
👉በተፈጥሮ ሳይንስ በወንድ ከ600 አጠቃላይ ውጤት 591.6 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው በአዳማ የሚገኘው የኦዳ ስፔሻል ቦርዲንግ ተማሪ ነው፡፡
👉583 በማምጣት በተፈጥሮ ሳይንስ 2ኛ እና ከሴቶች ቀዳሚ የሆነችው ደግሞ እንጅባራ ከተማ የሚገኘው የአገው ምድር ትምህርት ቤት ተማሪ ናት፡፡
👉በማህበራዊ ሳይንስ በወንድ ከፍተኛው 576.25 ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ አዳሪ ት/ቤት የተመዘገበ ሲሆን ÷ ከሴት ደግሞ 569.1 ቦሌ ሱፐር ሆሊ ሴቪዬር ት/ቤት ነው።
👉በዚህ ዓመት ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ 16.58 በመቶ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 8.33 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡
👉ተማሪዎችን ካስፈተኑ ት/ቤቶች መካከል 88 ት/ቤቶች 100% ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉ ሲሆን ÷ 565 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አላሳለፉም፡፡(ኤፍኤምሲ)

















