በተቋማዊ ልህቀት ረገድ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራር ለመዘርጋት የአመራርና የአፈጻጸም አቅም የሚገነባ ሲሆን፣ የፊዚካልና የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን በማዘመን ስማርት የሥልጠናና የምርምር ማዕከላት ይደራጃሉ። በተጨማሪም ስትራቴጂካዊ ኮሙኒኬሽንና አጋርነትን ማጠናከር የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ ተይዟል።
በሕግና ፍትሕ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ኢንስቲትዩቱ ችግር ፈቺ ጥናቶችን ለማሳደግ የውስጥ ተመራማሪዎችን አቅም የሚያጎለብት ሲሆን፣ በዳኝነትና ፍትሕ አካላት አቅም ግንባታ በኩል ደግሞ የቅድመ-ሥራና የሥራ ላይ ሥልጠናዎችን ጥራት በማሻሻል የዲጂታልና የኢ-ለርኒንግ አማራጮች ሰፊ ትኩረት ይሰጣቸዋል። በተመሳሳይ በፍላጎት ላይ የተመሠረቱ የሥልጠና ሞጁሎችን በማዘጋጀት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕግ አሠልጣኞችን ብቃት ለማሳደግ ታቅዷል።
በሌላ በኩል በሕግና ፍትሕ መረጃና ሪፎርም ዘርፍ ዘመናዊና ሀገር አቀፍ የሕግና ፍትሕ መረጃ ማዕከል በማልማት የመረጃ ክምችትን ለማሳደግ እንደሚሰራ የተጠቆመ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ የሕግ ትምህርት ሪፎርምን ጨምሮ የጋራ ሪፎርም ፕሮግራሞችን እንደሚተገብርና ለሥራዎቹ አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂካዊ ሀብት እንደሚያሰባስብም ተገልጿል።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች አስፈላጊውን ግብረ-መልስና ተጨማሪ አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ የቀጣይ በጀት ዓመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ከተቀመጡ በኋላ መድረኩ ተጠናቋል።
===================
ዘገባው:-የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት






















