ረቢኡል አወልን ኡለሞች ረቢኡ ነበውይ ይሉታል። ለምን ከተባለ ከነብያችን አለይሂ ወሰለም ህይወት ጋር በእጅጉ… — Seid Social — TG.ME

ረቢኡል አወልን ኡለሞች ረቢኡ ነበውይ ይሉታል። ለምን ከተባለ ከነብያችን አለይሂ ወሰለም ህይወት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ወር ነው። በእርሳቸው ሀያት የተፈፀሙ ትልልቅ ክስተቶች በአብዛኛው የተከሰቱት በረቢኡል አወል ነው።

1 የተወለዱት በረቢኡል አወል ነው!
2 ለመጀመሪያ ጊዜ የወህይ ህልም ያዩት በረቢኡል አወል ነው!
3 ወደ መዲና የተሰደዱት በረቢኡል አወል ነው!
4 ለመጀመሪያ ጊዜ መስጅዳቸውን መስጅዴ ኘበውይን እና መስጅደል ቁባንም የገነቡት በረቢኡል አወል ነው!
5 ኢላ ረፊቂል አእላ ብለውም ወደጌታቸው የሄዱበት ይህችን ዱኒያ የተሰናበቱበትም ወር ይሄው ወር ነው።

በአለማችን ላይ የነብያችንን ስም ለማጠልሸት ፤ የተላኩበትን የእዝነት መንገድ ስም ለማጥፋት ፤ ስብእናቸው ላይ ለመቅጠፍ ከ 60,000 በላይ መፅሀፍፍቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ፊልሞችና የካርቶን ምስሎች ተሰርተዋል።
ይሁን እንጅ በአለም ላይ አሁንም ቢሆን የእርሳቸውን ያክል ተወዳጅ ተፅእኖ ፈጣሪና ብዙዎች ገና ስማቸውን ሲጠሩ እንባቸው የሚጎርፍላቸው ሰው የለም!
እርሳቸው በፈጣሪም በፍጡርም እጅግ የተወደዱት ሰው ናቸው። በአለም ላይ የእርሳቸውን ስም ያክል መቶ ሚሊዮኖች ያወጡት ስም የለም። ስማቸው ይጣፍጣል!

የእዝነት መልእክታቸውን ላነበበ ማንም አለመማረክ አይችልም። አላህም የእርሳቸውን መላክ ዋና አላማ ሲናገር " ለአለማት እዝነት አድርገን እንጅ አላክንህም" ይላቸዋል።
ለፍጥረት ሁሉ አዛኝ ነበሩ። ለእንሰሳቱ ለሰው ዘርና ቀለም ፤ ሀይማኖትና ጎሳ ሳይለዩ የሚያዝኑ ሩህሩህ ነበሩ።
ያያቸው ሁሉ የሚወዳቸው ሰው ነበሩ። እስከዚህ ተብሎ ሊደካ የማይችል ውደታ!
የሚተናነሱ ነበሩ። ዛሂድ ነበሩ! ገመና ከታች አበሳሪ ነበሩ።
ማክበርን ጥንፍፍነትን ያስተማሩ የጨዋ ጨዋ ፤ የለጋስ ለጋስ!

ምስል :- በጣም የምወዳቸው ሸይኽ ሙሀመድ ሀሰን አልደደው
❤91👍15🥰5🥱3💔1
August 31, 2026 4.7K 21 15