የአከባቢና የዜጎች ሰላምና ደህንነት እንዲረጋገጥ በማድረግ ረገድ የፀጥታ ዘርፍ አካላት ድርሻ የጎላ እንደሆነ ተገለፀ
ነሀሴ 22/2018 ሳንኩራ ኮሙዩኒኬሽን
በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ከሚሊሻና ፖሊስ ተቋም ጋር በመሆን በ2018 የተሻ አፈጻጸም ማስመዝገብ ለቻሉ ባለሙያዎች በጋራ በመሆን ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡
የሀይማኖትና የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት የተካሄደው የዕውቅና መርሃ-ግብርን ያስጀመሩት የሳንኩራ ወረዳ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሱነሞ የአከባቢና የዜጎች ሰላምና ደህንነት እንዲረጋገጥ በማድረግ ረገድ የፀጥታ ዘርፍ አካላት ድርሻ የጎላ ነው ብለዋል፡፡
በየዘርፍ የሚሰጡ ተልዕኮዎችን በተገቢው በመወጣት ለአከባቢ ደህንነት መረጋገጥ በተሰራው ተቋማዊ ስራ ግንባር ቀደም ለሆኑ ባለሙያዎች ዕውቅና መስጠት የላቀ ተነሳሽነትን መፍጠር የሚችል መሆኑን አቶ ሸምሱ ተናግረዋል ፡፡
በመድረኩ ከሶስቱም ተቋም የተሻለ መፈጸም ለቻሉ ስራ ሂደቶችና ፈጻሚዎች እንዲሁም ለሀይማኖትና ለሀገር ሽማግሌዎች ዕውቅና የመስጠት መርሃ-ግብር ቴጥቷል፡፡
ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇
📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs
📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/
📌 የቴሌግራም Link፦
https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk
📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu
📌 ዩቲዩብ፦
https://www.youtube.com/@sankuratube
📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA
📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19
📌 ዌብሳይት https://sankuraprosperity.org.et/
