ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተሠጠ ማሳሰቢያ፦
ከሻሸመኔ ወደ አዳሚቱሉ የሚሄደው የኃይ ማስተላለፊያ መስመር ላይ የጥገና ሥራ የሚከናወን በመሆኑ አርብ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ በአሰላ፣ በአዳሚቱሉ፣ በቡታጅራ፣ በወራቤ፣ በቡኢ እና አካባቢው ኤሌክትሪክ ተቋርጦ ስለሚቆይ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል!!
(መረጃውን ያደረሰን የወራቤ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ነው)