በሴቶች ማህበር እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ
ነሀሴ 17/2018 የሳንኩራ ኮሙኒኬሽን
በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ የሴቶች ማህበር የ2018 የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዕቅድ ዙሪያ ከማህበሩ አባላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡
ማህበሩ ያካሄደው መድረክ በ2018 በጀት ዓመት በማህበሩ የተሰሩ ተግባራትን በመገምገም በበጀት ዓመቱ ለመስራት በታቀዱ ዕዶች ላይ የጋራ መግባባት ለመድረስ ያለመ ነው፡፡
በመድረኩ የ2018 የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዕቅድ በማህበሩ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሰኪና ሞሳ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡
በባለፈው በጀት ዓመት በሴቶች ማህበር በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገብ ስለመቻሉ በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን የስልጤ ዞን ሴቶች ማህበር ባካሄደው ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ማጠቃለያ መድረክ ማህበር 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ መሆን እንደቻለ ተብራርቷል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት በተሰራው ስራ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ👇👇
📌ፌስቡክ፦ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs
📌 ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/
📌 የቴሌግራም Link፦
https://t.me +7_qexDRrC-Q2ODhk
📌ቲክቶክ፦ http://tiktok.com/@sankurawerdacommu
📌 ዩቲዩብ፦
https://www.youtube.com/@sankuratube
📌 ኢንስታግራም፡https://www.instagram.com/p/CnUbPjmtA42/?igshid=YmE3OTBmZTA
📌 ቲውተር፦https://x.com/SankuraCom/status/1942288703126180135?t=qhKGvP0NqcD2CJoSh9yt9g&s=19
📌 ዌብሳይት https://sankuraprosperity.org.et/
August 23, 2026 226