የሻዕቢያ ቴርሞሜትር የሆነው ኪዳነ አመነ አዲስ ጩኸት እና በህወሓት ካምፕ የገባው ከባድ ጭንቀት! 🚨 ኪዳነ… — Mehal media — TG.ME

🚨 የሻዕቢያ ቴርሞሜትር የሆነው ኪዳነ አመነ አዲስ ጩኸት እና በህወሓት ካምፕ የገባው ከባድ ጭንቀት! 🚨

ኪዳነ አመነን ስትሰሙት የራሱን እሳቤ ሳይሆን የፋይናንስ ምንጩን እና የጌታውን (የሻዕቢያን) የልብ ትርታ ነው የሚያንጸባርቀው። ዛሬ የሻዕቢያን አእምሮ በኪዳነ አንደበት ስንመዝነው፣ በአስመራ ኃይለኛ ቅዝቃዜ እና ድንጋጤ መፈጠሩን በግልጽ እናያለን።

📌 በአስመራ እና በመቀሌ የተፈጠረው የፖለቲካ መናወጥ፦

* 📍 የመጀመሪያው የሻዕቢያ ድንጋጤ፦ የትግራይ ወታደራዊ ኮማንድ "የመዋጋት አቅም የለንም፤ ሻዕቢያም ሆነ ፋኖ ቁምነገር ያለው እርዳታ ሊሰጡን አይችሉም" ብሎ መወሰኑ ሻዕቢያን አርበድብዶታል። ሻዕቢያም ይህንን ሽንፈት ለማከም ታማኝ ሰዎችን የሰበሰበ አዲስ ኮማንድ ፖስት ለማቋቋም እየዳከረ ይገኛል።
* 📍 ሁለተኛው የሻዕቢያ ድንጋጤ፦ የደብረጽዮን ቡድን ከአውሮፓ፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከአሜሪካ ጋር የሚያደርገው ሚስጥራዊ የሰላም ድርድር ነው። የትራምፕ አስተዳደር ልዑክ (ፍራንክ ጋርሺያ) ጥብቅ መልእክት ይዘው አዲስ አበባ መምጣታቸው ሻዕቢያን ስላስጨነቀው፤ ኪዳነን በመላክ "እባክሽን የሻዕቢያ መከላከያ የምትሆኚበትን የጦርነት መንገድ ትተሽ ብቻሽን ወደ ሰላም ድርድር እንዳትገቢ" በማለት ህወሓትን እየተማጸነ ይገኛል።
* 📍 የድሮን ቅጥቀጣው እና የኪዳነ ባዶ ፉከራ፦ የህወሓት ሰራዊት አንገቱን ብቅ ባደረገ ቁጥር በኢትዮጵያ አየር ኃይል ድሮኖች ፊጥ እያለ ባለበት እና ህወሓት በጩኸት እያቃሰተች ባለችበት በአሁኑ ሰዓት፤ ኪዳነ "ብልጽግናን ለማስወገድ ፐርፌክት ጊዜ አሁን ነው" ይላል። የሚቀጠቀጠው የልደት ፈንድሻ ይመስል!
* 📍 የትግራይ ህዝብ እርምጃ፦ ኪዳነ ለህወሓት ሞራል እንዲሰጣት ይለምናል፤ የትግራይ ህዝብ ግን ሞራል ሊሰጣት ቀርቶ፣ በጀርባው ላይ ወድቃ እንዳታሰናክለው መንደሩን ትቶላት እየራቀ ይገኛል።
* 📍 የኪዳነ አረመኔነት፦ ኪዳነ ከትግራይ ውጭ በአዳማ እና በተለያዩ አካባቢዎች በሰላም የሚኖረውን ትግራዋይ በሰላይነት እንዲጠረጠርና ጥቃት እንዲደርስበት የሚያደርገው ቅስቀሳ፣ የጌቶቹን ህሊና-ቢስነት እና አረመኔነት ፍንትው አድርጎ ያሳያል።

*(የመሐል ሚዲያ ማስታወሻ)*፦ ሻዕቢያን እና ህወሓትን እያብረከረካቸው ያለው ይህ የሰላም ፍላጎት እና የፖለቲካ ማዕበል፤ ሁለቱንም የጥፋት ኃይሎች በአንድ ጊዜ ውጦ የሚያጠፋ ኃይለኛ ጎርፍ መሆኑ አይቀርም!

📲 ይህንን ጥልቅ ትንታኔ ሁሉም እንዲገነዘበው፤ ፖስቱን አሁኑኑ ሼር (Share) በማድረግ ያጋሩ!

#መሐልሚዲያ #MehalMedia #Tigray #Ethiopia #ሰበርመረጃ #Share
❤28👍7
September 2, 2026 3.6K 1