አንበሳ ባንክ እናመሠግናለን‼
በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ሰለዋ ወረዳ ደላ ከተማ በሚገኘው የአንበሳ ባንክ ቅርንጫፍ የ7 ዓመት ጥበቃ ሠራተኛ የሆኑት አቶ ሰይፈ ተስፋዬ ካሕሳይ፣ በ46 ዓመታቸው በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 320.25 ነጥብ በማምጣት ወደ ዩኒቨርሲቲ አልፈዋል።
ለዚህ አስደናቂ ስኬታቸው የባንኩ ሥራ አመራር የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ያስተላለፈ ሲሆን፡-
📌ሙሉ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ወጪያቸውን ለመሸፈን፣
📌በትምህርት ላይ ሳሉ ወርሃዊ ደመወዛቸው ሙሉ በሙሉ ለቤተሰባቸው እንዲከፈል፣
📌ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁም ባንኩ በተገቢው የሥራ ዘርፍ በቋሚነት እንዲመድባቸው ውሳኔ አስተላልፏል።
ለዚህ መልካም ውሳኔ አመስግነናል‼

101
32
13August 29, 2026 4.7K 6