መዝሙረ ተዋህዶ: post #379 — TG.ME

ሕማማት_ረቡዕ
የመልካም መአዛ ቀን ይባላል፦ይህም ቃል ጌታ በስምኦን ዘለምፅ ቤት በእግድነት ሳለ ማርያም (እንተእፍረት) ባለ ሽቱዋ ማርያም በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ በፀጉሩ (በራሱ) ላይ ስለቀባችው ነው።

የእንባ ቀንም ይባላል፦ይህም ማለት ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ሀጥያቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለች እና ያጠበችውንም በፅጉሩዋ አብሳዋለች እና።
ጌታ ይቅር ባይ አምላክ ነውና ልጀ ሆይ ሀጥያትሽ ተሰርዬልሻልና በሰላም ወደ ቤትሽ ሂጅ አላት።
አቤቱ ይቅር በለን እራራልንም ለብርሀነ ትንሳየህ በሰላም አድርሰን
April 12, 2023 9.8K 3