መዝሙረ ተዋህዶ: post #382 — TG.ME

እሁድ፦ ዳግም ትንሣኤ ይባላል፦

"…ከመጀመሪያው ትንሣኤ ቀጥሎ ያለው የመጀመሪያው ሳምንት በስምንተኛው ቀን የምናገኘው እሁድ ዳግም ትንሣኤ ይባላል። በዚህ ዕለት ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤው ፍጹም መሆኑን ለማረጋገጥ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱን በማሰብ ዕለቱ ይታሰብ፣ ይከበርበርም ዘንድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርታለች።

"…ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፥ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ። ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቆሞ፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው። ከዚያም በኋላ ቶማስን፦ ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው። ቶማስም፦ ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት። ኢየሱስም፦ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው። ዮሐ 20፥ 26-29።

"…ይህ ዕለት እንደ ሐዋርያው ቶማስ ላሉ ትንሣኤውን ለተጠራጠሩ ሰዎች የተወጋውን ጎኑን ተመልክተው እና ደስሰው በእውነት የተነሣው ጌታ እሱ መሆኑን በእርግጠኝነት ያመኑበት ዕለት ነው። የዛሬው እሁድ የዕለተ ትንሣኤ ስምንተኛ ቀን አግብዖተ ግብር ዳግም ትንሣኤም ይባላል። “እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤” ዮሐ 17፥4 ብሎ በሐዋርያቱ ፊት ለመጨረሻ ጊዜ ከእርገቱ በፊት በቅዱስ ወንጌል ያልተጻፉ ድንቆችን ያደረገበትም እለት ነው።“ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤” ዮሐ 20፥30

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም።
April 23, 2023 12.5K 6