#እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በጌቴ ሴማኒ በአትክልቱ ቦታ ሳለ ጸሐፍት ፉሪሳውያን በአይሁድ ሸንጎ ውሳኔ መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ያለበትን ለጠቆመ ወሮታ እንከፍላለን ባሉት መሠረት ከዳተኛው ይሁዳ በዚህ ምሴተ ሐሙስ የካህናት አለቆችንና ፈሪሳውያንን እንዲሁም ኢየሱስን ለመያዝ የተመደቡት የሮማ ቄሳር ወታደሮችን በመምራት ኢየሱስ በጸሎት ከሚያሳልፍበት ከጌቴ ሴማኒ ይዟቸው እየመጣ ነው ። እግዚእነ ኢየሱስም ሁሉን አዋቂ አምላክ ነውና ይሁዳ የሮማ ቄሳር ወታደሮችንና ፈሪሳውያንን እየመራ ሊያሲዘው እየመጣ መሆኑን ለደቀ መዛሙርቱ " ገናም ሲናገራሳቸው እነሆም ቆመጥ የያዙ የሮማ ቄሳር ወታደሮች ወደ አትክልት ስፍራ ገቡ። ይሁዳም ከፈሪሳውያን ጋር በተነጋገረው የያዙት ምልክት መሠረት ሊስመው ወደ ኢየሱስ ቀረበ ፣ ኢየሱስም በመሳም አሳልፈህ ልትሰጠኝ መጣህን?? አለው ። የሮማ ቄሳር ወታደሮችም እግዚእነ ኢየሱስን ያዙት።
#ሰባተኛው ሰዓት ሌሊት ሲሆን የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎችና ፈሪሳውያን ኢየሱስ እንደተያዘ እንደተያዘ ወደ ተሻረው የአይሁድ ሊቀ ካህናት እንዲወሰድ የያዙትን የሮማ ቄሳር ወታደሮችን መከሩ ። የአይሁድ ካህናት ተንኮል የረቀቀ ነበር ። በዚህን ወቅት በሕጋቸው በማይፈቀድ ሁኔታ ሁለት ሊቃነ ካህናት ነበራቸው፣ አንዱ የይስሙላ ሲሆን በሕግ ግን የተሻረ ነበር ። ከሥልጣኑ የተሻረው ሊቀ ካህናት ሐና ይባላል ። ይህ የተሻረው ሊቀ ካህናት ሌሊትም እሠራለሁ ባይ ነበርና አይሁድ ሆን ብለው ውሳኔ መስጠት ወደ ማይችለው ሊቀ ካህናት ዘንድ ኢየሱስን አስወሰዱት። (ዮሐ.18:23፤ማቴ.27:26) ሐናም ይሄን ጉዳይ እኔ ማየት አልችልም ብሎ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ መራው ።
#ይሁንና የአይሁድ ሸንጓቸው ሥራ የሚጀምረው ሲነጋ ጠዋት ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ባለው አደባባይ ላይ ሆኖ በሊቀ ካህናቱ ቀያፋ እየተመራ ስለሚካሄድ የሮማ ቄሳር ወታደሮች ኢየሱስን ወደየት መውሰድ እንዳለባቸው ባለማወቃቸው ኢየሱስ ክርስቶስን ሊያንገላቱት ሆነ ።
April 13, 2023 12.2K 6