መዝሙረ ተዋህዶ: post #376 — TG.ME

☞ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ
☞ማክሰኞ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡
☞ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት ሹመትን ወይም ሥልጣንን
ለሰው ልጅ የሠጠ ጌታችን ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና
የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡
☞ጥያቄውም"ከምድራውያን ነገሥታት ከሌዋውን ካህናት ያይደለህ ትምህርት
ማስተማር፤ተአምራት ማድረግ፤ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ
ይህንንስ ሥልጣን ማን ሠጠህ የሚል ነበር፡፡
☞እርሱም ሲመልስ እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኃለሁ፤ እናንተም ብትነገሩኝ
በማን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኀለሁ፡፡
☞"ዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበር ከሰማይ ነው ወይስ ከሰው በእግዚአብሔር
ፈቃድ ወይስ በሰው ፈቃድ አላችው፡፡
☞እነርሱም"ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤"ከሰው ብንል
ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን
እንፈራለን ተባብለው ከወዴት እንደሆነ እናውቅም"ብለው መለሱለት፡፡
እርሱም"እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማልደርግ አልነግራችሁም
አላቸው፡፡(ማቴ 21-12-14)
☞በተጨማሪም በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምሕርት ቀንም
ይባላል፡፡(ማቴ 21-23፥28)
April 10, 2023 9.5K 3