ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ
✍️✍️✍️✍️
ብዕር ባስለቀሰው
የቅኔ ፊደላት እምባህን አብሰህ
ቀን እስኪያልፍ ቢያለፋም
የከፋው ገፅህን በፈገግታ አልብሰህ
ወርቅ ማንነትህ
በመዳብ የቃኙት ክብርህን ባይለካም
ጠቢብ ካደላበት
የውስጥህን ዓለም ህሊናህ ባይረካም
ከፅናት ማህደር
ጠብቀህ ያኖርከው ጥበብ ቢገነፍል
የእውነት ልብ እንዳይሞት
ስጋ ይንገላታል ነፍስ ዋጋ ሲከፍል

13June 28, 2026 1.7K 4