( ያሬዳዊ ግጥም ) ያሬድ ከበደ
ፖለቲካ አይደለም
✍️✍️✍️✍️
ትዝታ አንቺ ሆዬ
በባቲና አምባሰል ቃኝተህ አፈ ሙዙን
ከዘመነ ጊልዶ
አሻግረህ እንድናይ ዘመነ ካሙዙን
ሰምና ወርቅ ቅኔ
ህልምም ይሁን ቅዠት ነውና እንደ ፈችው
የፓርላማን አባል
ከእቅልፉ ቀስቅሳ ጥበብ ከጠራችው
በቀን ሶስት ጊዜ
ባስማት የሚመግብ እስኪሰጠው መሪ
የፖለቲካን መልክ
በከፊልም ቢሆን መቀየር ከቻለ አንድ አቀናባሪ
የነ እከሌን ዘፈን
ሲሰማ ለኖረ ዳባ ለባሽ ጆሮ ምን ቢሰቀጥጥም
መንግስት ዜማ ካለው
ላድማጭ ነፃነት ሲል ህዝብ ይፅፋል ግጥም
11
2
1April 1, 2026 2.8K 2