ለላይኛው ሰማይ፣ ለመኖሪያ አድራሻህ
ፀሎት እንልካለን፣ መልሱን ግን እንዳሻህ
ብቻ እንድንፅናና…
ተመላላሽ ሞገድ መሃላችን አፅና
‘ለምን?’ ማለት ጥሩ…
ሺ ምልጃዎቻችን በዚያው ከሚቀሩ
መቼስ በዓለም ዙሪያ…
ወይ ስራ በዝቶበት
ወይ ሲጨፍር አድሮ፣ አናቱ ዙሮበት
ሳይፀልይ ያደረ ይኖራል አንድ ሰው
ጠይቀንህ የለ? መልሱን ለሱ አድርሰው!
እኛም እንላለን…
‘ፀሎቴ መች ቀረ?
ሞገድ ወስዶ ወስዶ አቅጣጫ አስቶታል
‘ቢሆንልኝ’ ያልኩት፣ ዘመዴ ደርሶታል።
#ደሱ