ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ ✍️✍️✍️✍️ ታሳ ጋሞ 😭😭😭😭😭 😭😭😭😭😭😭 እንደ ሐምሌ ወራት… — ግጥም 🇪🇹 — TG.ME

ያሬዳዊ ግጥም) ያሬድ ከበደ
✍️✍️✍️✍️

ታሳ ጋሞ
😭😭😭😭😭
😭😭😭😭😭😭

እንደ ሐምሌ ወራት
የሀዘን ጥል አጥልቶ ከጋሞ ሰማይ ስር

ሞትም ከነ ጓዙ
እያጉረመረመ ቁልቁል ጣት ሲቀስር

መቼም አንዳንድ ቀን
ሰኔና ሰኞ አይነት እንደ ገጠመ እጣው

ሰው ፈልጌ ብሄድ ዛሬ ግን ሰው አጣው
አውድማውን ብቃኝ በሬ'ሳላይ መጣው

ታዲያ በዚህ መሀል,,,,,

ያየሁትን ሁሉ ውስጤ አላምን አለኝ
ደስታን የሚሰጥ ህዝብ በሀዘን ሲቀበለኝ

ትህትና ፍቅራቸው
መልካምነታቸው እጅጉን የበዛ

እንደ ባህል ወጉ
ፈትሎና ሸምኖ ሚያለብሰው ድንጉዛ

ዛሬ ምን ገጠመው
ቅን ልቡ ሲሰበር በሀዘን ስንክሳር

ጌታ ሆይ እባክህ በቶሎ ታረቀን
ይላል የጋሞ ህዝብ ቀንጥሶ እርጥብ ሳር
❤5😭2🥰1👏1
March 15, 2026 2.5K 1